
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 1/2017(ኢዜአ)፦ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) በአፋር ክልል አዋሽ ሰባት በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር መስመር ደህንነት ዙሪያ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ውይይት እድርገዋል።
ሚኒስትሩ በተለይ በቅርብ ጊዜ በባቡሩ ኤሌክትሪክ መስመር ላይ ጉዳት እና ስርቆት መድረሱን ተከትሎ ችግሩን ለመፍታት ከአካባቢው ሃይማኖት አባቶች፣ ከጎሳ መሪዎች፣ ከፀጥታ አካላት እና ከተለያዩ ስራ ኃላፊዎች ጋር መክረዋል።
የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር መስመር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታትና ባቡሩን በሙሉ አቅም መጠቀም እንዲቻል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው ችግሩ እንዲፈጠር ያደረጉ አካላትን በትብብር የማጥራት ስራ መከናወን እዳለበት ገልጸዋል።
በባቡር መስመሩ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ከፌዴራል መንግስት፣ ከክልል መንግስታት፣ ከፀጥታ አካላት፣ ከኢትዮጵያ መብራት ሀይል እና ከሌሎች አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በባቡር መስመሩ ላይ ጉዳት በማድረስ ስርቆት በሚፈፅሙ አካላት ላይ ከመንግሥት ጎን በመሆን የማጋለጥ ስራ እያከናወኑ መሆኑን መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026