አሶሳ፤ ሚያዝያ 1/2017(ኢዜአ):- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ይበልጥ ለማሳደግ በቅንጅት ይሰራል ሲሉ የዘርፉ አመራሮች ተናገሩ።
ዘጠነኛው ክልል አቀፍ የግብርና ዘርፍ ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ የዘርፉ ጠንካራ እና ደካማ ጎን የተገመገመ ሲሆን ለ2017/18 የምርት ዘመን አርሶ አደሩ የግብርና ስራውን በተሻለ መልኩ መተግበር እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል።
ኢዜአ ያነጋገራቸው የመድረኩ ተሳታፊዎች በክልሉ የግብርና ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
ከተሳታፊዎቹ መካከል የመተከል ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አባይ በክልሉ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረጉ ጥረቶች ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።
መድረኩም የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የግብርና ዘርፉ እንዲዘምን እና የአርሶ አደሩ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ግብዓት የተወሰደበት ነው ብለዋል።
የአሶሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ደስታ በቀለ በበኩላቸው በክልሉ የግብርናውን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ ማዕከሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ እና በማላመድ የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።
ማዕከሉ በቅርቡ ያወጣቸውን የበርበሬ እና ከርከዴ ምርቶች ወደ አርሶ አደሩ ለማድረስ እየሰራ መሆኑን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ በሰሊጥ እና በማሽላ ምርቶች ላይም በስፋት ለመስራት ዕቅድ መያዙን ጠቁመዋል።
ለስራው ስኬታማነት ከግብርና ቢሮ ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውን በመጠቆም።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 3 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር ማሳ ለእርሻ ተስማሚ ቢሆንም እስካሁን ማልማት የተቻለው 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር ማሳ ብቻ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በክልሉ ግብርና ቢሮ የግብርና ኤክስቴንሽን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም አብዱልጀሊል ናቸው።
አርሶ አደሩ የሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የግብርና ስራውን በስፋት እንዲያከናውን ለማድረግ ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
በአሁኑ ሰዓት በክልሉ የምርጥ ዘር እና የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት መኖሩን ጠቅሰው አርሶ አደሩ በወቅቱ እንዲጠቀም እና የእርሻ ማሳውን እንዲያዘጋጅ አሳስበዋል።
ዘጠነኛው ክልል አቀፍ የግብርና ዘርፍ የባለድርሻ አካላት መድረክ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የግብርናው ዘርፍ ባለድርሻ አካላት እና የምርምር ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ተካሂዷል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025