የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የጋምቤላ ከተማ የኮሪደር ልማት ስኬታማ እንዲሆን የሁሉንም ተሳትፎ ይፈልጋል - ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ

Apr 11, 2025

IDOPRESS

ጋምቤላ፤ሚያዝያ 2/2017(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ከተማ ለተጀመረው የኮሪደር ልማት ስኬታማነት የህዝቡና የባለሀብቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ዓለሚቱ ኡሞድ ገለጹ።

የጋምቤላ ከተማ የኮሪደር ልማት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ተካሂዷል።


ርዕሰ መስተዳደሯ በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ እንዳሉት የከተሞችን ልማት ለማዘመንና ለኑሮ ምቹና ውብ ለማድረግ ለተጀመረው የኮሪደር ልማት መሳካት የህዝቡና የባለሃብቱ ድጋፍና ትብብር ሊጠናከር ይገባል።

የከተሞች ልማት መዘመን ለገጽታ ግንባታና ለኑሮ ምቹ ከመሆን ባለፈ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪውና ለስራ እድል ፈጠራ ጭምር የጎላ ፋይዳ ያለው መሆኑንም ተናግረዋል።


በመሆኑም የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች በመንግስት ብቻ ስኬታማ ስለማይሆኑ የህብረተሰቡና የባለሀብቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ድጋፍ ወሳኝ ነው ብለዋል።

የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሰይመን ሙን(ዶ/ር) በበኩላቸው መንግስት የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከጀመራቸው ስራዎች መካከል የኮርደር ልማት አንዱ ነው ብለዋል።


ይህን ታሳቢ በማድረግ ከተማ አስተዳደሩ የጋምቤላ ከተማን ልማት በማዘመን ውብና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።

በገቢ በማስጀመሪያ መረሃ ግብሩ ላይ የክልሉ፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ባለሃብቶች ተገኝተዋል ።

በጋምቤላ ከተማ በመጀመሪያ ዙር በአራት አቅጣጫ 14 ኪሎ ሜትር የሚሸፋን የኮሪደር ልማት ተጀምሯል ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025