
አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 2/2017 (ኢዜአ):-ባለፉት ዘጠኝ ወራት 1 ሚሊዮን 422 ሺህ በላይ ዜጎች በገበያ መረጃ ስርዓት መመዝገባቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ስድስተኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አራተኛ ዓመት የስራ ዘመን 23ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደ ሲሆን፤የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን አዳምጧል ።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ከሚል በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ ሚኒስቴሩ በ2017 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ልማት፣በኢንዱስትሪ ሰላም እንዲሁም በተቋም ግንባታ ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ተግባራት አከናውኗል።
ተቋማዊ የሪፎርም ተግባራትን እንደምቹ ሁኔታ በመውሰድ እቅድ በማዘጋጀት በየዘርፉ ያለውን መዋቅር በመጠቀም ሰፋ ያለ የባለድርሻ ተሳትፎን በማረጋገጥ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራት የዘርፉን ተልዕኮ ለመፈፀም የተሻለ መደላድል መፍጠር መቻሉንም ጠቁመዋል።
በሚኒስቴሩ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የተቋማዊ ሪፎርም ሥራዎችን በማፅናት ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል የስልጠናና ምክክር መድረክ መካሄዱን ተናግረዋል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት 1 ሚሊዮን 422 ሺህ በላይ ዜጎች በገበያ መረጃ ስርዓት መመዝገባቸውን ገልፀው፤ ስርዓቱ በአገር ውስጥ የሥራ እድል ለመፍጠር፣ለውጭ አገር የስራ ስምሪት እና ሌሎች አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን አመልክተዋል።
በዚሁ ስርዓት 110 የፖሊ ቴክኒክ ተቋማት የተማሪዎች ቅበላ ለማከናወን የሚያስችል ስራ መጀመሩንም ተናግረዋል።
ለአገር ውስጥና ውጭ አገር ስራ ስምሪት 3 ሚሊየን 300 ሺህ በላይ ዜጎችን የአጫጭር ስልጠና መስጠት ታቅዶ 3 ሚሊየን 170 ሺህ በላይ ዜጎችን ማሰልጠን መቻሉንም ገልፀዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026