የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ጎረቤት ሀገራት በቀጣናዊ የትብብር መንፈስ ለኢትዮጵያ የባህር በር ሊሰጡ ይገባል-ኬንያዊው የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪ

Apr 11, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 2/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የጀመረችው እንቅስቃሴ የጎረቤት ሀገራት በቀጣናዊ ትብብር መንፈስ ሊሰጡ እንደሚገባ ኬንያዊው የዓለም አቀፍ ግንኙነትና የደህንነት ጉዳዮች ተመራማሪ ኤድጋር ጊቱዋ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡


በኬንያ ናይሮቢ በሚገኘው ስትራትሞር ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ኤድጋር ጊቱዋ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ በአፍሪካ ቀንድ እየተበራከቱ የመጡ የኃያላን ሀገራት የጦር ሰፈሮችና የባህር ወደቦች ጥቅምና ጉዳት እንዲሁም የባህር በርን በማስመልከት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡


በማብራሪያቸውም የዓለም ኃያላን ሀገራትን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ከ12 በላይ የጦር ሰፈሮች መኖራቸውን ጠቁመው፥ በዚህም ቀጣናው በዓለም ከፍተኛ ወታደራዊ ኃይል ያለበት ቀጠና ሆኗል ብለዋል፡፡


እነዚህ የውጭ ኃይሎች በቀጣናው የራሳቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ጂኦፖለቲካል እና የደህንነት ፋላጎት እንዳላቸው ጠቅሰዋል፡፡


በቀጣናው የውጭ ኃይሎች ወታደራዊ ሰፈሮችን ማስፋፋታቸው በሁለት በኩል የተሳለ ቢላ ነው ያሉት ዶክተር ኤድጋር፥ ይህም አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡


በአንድ በኩል ሽብርተኝነትን ጨምሮ በባህር ላይ የተደራጁ ወንበዴዎችን ለመከላከል ትልቅ እገዛ በማድረግ አዎንታዊ ሚና ያለውን ያህል፥ በአሉታዊ ጎኑ ለቀጣናው ሀገራት የደህንነት ስጋት እንደሚፈጥር አንስተዋል፡፡


የውጭ ኃያላን ሀገራት በቀጣናው ያላቸውን ፍላጎት በኃይል ለማሳካት የጦር ሰፈሮችን ጫና መፍጠሪያና ግጭት መቀስቀሻ አድርገው ሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉም ጠቁመዋል።


ዶክተር ኤድጋር ጊቱዋ በቀጣናው እየተስፋፉ ያሉ የባህር ወደቦችን ጉዳይ ተስፋና ስጋት አላቸው በሚል በሁለት አውድ ተመልክተዋቸዋል።


በየጊዜው የባህር ወደቦች መጨመር ለአፍሪካውያን ሀገራት አዳዲስ የንግድ መስመሮችን በመክፈትና ወደ አውሮፓና ኤዥያ ገበያ የሚልኳቸውን ምርቶች በመጨመር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።


ሆኖም የውጭ ኃይሎች በቀጣናው መኖራቸው ትልቅ ስጋት መደቀኑን ጠቅሰው፥ እነዚህ ኃይላት ወደቦችን ሙሉ ለሙሉ የሚቆጣጠሩ ከሆነ የአፍሪካ ሀገራት ሉዓላዊነትና የኢኮኖሚ ሁኔታ አደጋ ላይ ይወድቃል ብለዋል።


ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ለባህር በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኝና በዓለም ትልቋ የባህር በር የሌላት ሀገር ናት ብለዋል።


በአንጻሩ በብዙ ሺህ ማይል ርቀት የሚገኙ የውጭ ኃይሎች በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የንግድና ወታደራዊ ወደብ ባለቤት መሆናቸውንም አንስተዋል።


በመሆኑም በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ ጎረቤት ሀገራት በፓንአፍሪካኒዝም መንፈስና በቀጣናዊ የትብብር መርህ ለኢትዮጵያ የባህር በር ሊሰጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025