አምቦ፤ሚያዚያ 2/2017( ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በስፋት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።
በዞኑ ቶኬ ኩታዬ ወረዳ አመራሮችና ህብረተሰቡ የተሳተፉበት በስድስት ሄክታር መሬት ላይ የሙዝ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተከናውኗል።
በችግኝ ተካላ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የምዕራብ ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳደሪ አቶ አበበ ጨመዳ እንደገለጹት፥ በዞኑ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት እምብዛም የተለመደ አይደለም።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ግን የክልሉ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ከጥራጥሬ ሰብሎች ባሻገር በአትልትና ፍራፍሬ ልማት የተሻለ እንቅስቃሴ ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል።
የአትክልትና ፍራፍሬ ልማቱ በክረምት ዝናብ ብቻ ሳይሆን በበጋ መስኖም በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፥ በዚህ ዓመትም በበጋ መስኖ 145 ሺህ የሙዝ ችግኝ መተከሉን አረጋግጠዋል።
የዞኑ ኢርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተረፈ አራርሳ በበኩላቸው በዞኑ በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች የሙዝ ችግኝን ጨምሮ ሌሎች የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኝ ተከላ ሲካሄድ መቆየቱን ጠቅሰዋል።
ከዚህ በፊት የዞኑ አርሶ አደሮች በዓመት አንዴ ብቻ የጥራጥሬ ሰብሎችን ያመርቱ እንደነበር ያነሱት ሀላፊው ባለፉት ሶስት ዓመታት 19 ሚሊየን የአትልትና ፍራፍሬ ችግኝ መተከሉን ገልጸዋል።
ዘንድሮም 22 ሚሊየን የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኝ ለመትከል ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ስራው ተጠናክሮ መጠቀሉን አስረድተዋል።
ከአርሶ አደሮች ባለፈ ወጣቶችን በማህበር በማደራጀት በልማቱ እንዲሳተፉ እየተደረገ መሆኑን አክለዋል።
የወረዳው አርሶ አደሮች የሙዝ ልማት ውስጥ እንዲሳተፉ በተደረገው ጥረት አሁን ላይ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎች መታየታቸውን የተናገሩት ደግሞ የቶኬ ኩታዬ ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽህፈት ቤት የቡና እና ሆርቲካልቸር ልማት ቡድን መሪ አቶ አብዲሳ ሂርጳሳ ናቸው።
በአሁኑ ወቅትም የወረዳው አርሶ አደሮች ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በትልትና ፍራፍሬ ልማት በስፋት እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረዋል።
በአትልትትና ፍራፍሬ ማልማት የጀመሩ አርሶ አደሮችም ልማቱ የተሻለ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው ተስፋ በማድርግ በስራው እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ ወቅት በክላስተር ተደራጅተው ሙዝን ጨምሮ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ማልማት መጀመራቸውን ገልጸው የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽህፈት ቤትም አስፈላጊ ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን አንስተዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025