
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 6/2017(ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ 215 ሺህ ቶን ማር መመረቱን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የሌማት ትሩፋት መርኃ ግብር ከተጀመረ ወዲህ ከማር ምርት ከፍተኛ ውጤት መገኘቱን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ(ዶ/ር) ተናግረዋል።
በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 210 ሺህ ቶን ማር ለማምረት እቅድ መያዙን አስታውሰው በአፈጻጸም ረገድ 215 ሺህ ቶን ማር በማምረት ከእቅድ በላይ አፈጻጸም መመዝገቡን ገልጸዋል።
በሌማት ትሩፋት መርኃ ግብር ጥሩ ውጤት ከተገኘባቸው ምርቶች አንዱ ማር መሆኑንም አስታውቀዋል።

አፈጻጸሙን የበለጠ ለማሳደግ ባህላዊ ቀፎችን ወደ ዘመናዊ ቀፎ የመለወጥ ሥራ በስፋት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ከአንድ ባህላዊ ቀፎ የሚገኘው ምርት ከ10 ኪሎ ግራም እንደማይበልጥ አንስተው ከዘመናዊ ቀፎ ግን ከ35 ኪሎ ግራም በላይ ምርት እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ዘመናዊ ቀፎ የማር ምርት በብዛትና በጥራት እንዲጨምር ማስቻሉን ጠቅሰው ባለፉት ዘጠኝ ወራት 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ዘመናዊ እና የሽግግር የንብ ቀፎ ለህብረተሰቡ መሰራጫቱን ገልጸዋል።
በሀገሪቱ በተለመደው ባህላዊ የንብ ማነብ ስራ ብዙ ምርት እንደማይገኝ በማስታወስ ምርታማነትን ለማሳደግ ለንብ አናቢዎች በስፋት ዘመናዊ የንብ ቀፎ እየተከፋፈለ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።
በተጠናከረ መንገድ እየተተገበረ በሚገኘው ዘመናዊ የንብ ማነብ ስራ ንብ አንቢዎች ከፍተኛ ገቢ እያገኙ መሆኑን ተናግረዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026