
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 6/2017(ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ከዚያም በላይ አፈጻጸም እያስመዘገቡ መሆኑን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ(ዶ/ር) ገለጹ።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት የሦስተኛው ሩብ ዓመት የ100 ቀናትና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራ የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም ግምገማ ተካሂዷል።
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ(ዶ/ር)፥ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሁሉም መስኮች ከዕቅድ በላይ አፈጻጸም መመዝገቡን አብራርተዋል።
አጠቃላይ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚሳካም የተመዘገቡ ውጤቶች አመላካች መሆናቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፥ በመስኖ ልማት ዘርፍም አመርቂ አፈጻጸም መኖሩን ጠቅሰዋል።
ከሀገራዊ ለውጡ በፊት የመስኖ ፕሮጀክቶች ለረጅም ጊዜ በመጓተት በህብረተሰቡ በኩል ቅሬታ ሲያስነሱ እንደነበር ገልጸው፤ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም በጣም ደካማ የነበረ መሆኑን አስታውሰዋል።
በሪፎርሙም የፕሮጀክት አፈጻጸምና አስተዳደርን በማሻሻል ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን ጠቅሰው፥ በበጀት ዓመቱ የመስኖ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ዕቅድና ከዚያም በላይ አፈጻጸም መመዝገቡን ገልጸዋል።
በዚህ ዓመት የሚጠናቀቁ የመስኖ ግድቦችን በፍጥነት እውን በማድረግ ወደ ሥራ መግባታቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፥ ለአብነትም የጎዴ የመስኖ ፕሮጀክትን ጠቅሰዋል።
የወልመል መስኖ ልማት ፕሮጀክት በሚቀጥለው ወር ተመርቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ በማንሳት፥ የከሰም ግድብ ፕሮጀክትንም ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በቀጣይ የተመዘገበውነ ስኬት በማጠናከር ለላቀ ውጤት እንተጋለን ሲሉም ነው ሚኒስትሩ በአጽንኦት የተናገሩት።
የፌደራል መንግሥት ትላልቅ የመስኖ ፕሮጀክቶችን እየገነባ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ፕሮጀክቶች እንዳይጎዱና እንዳይስተጓጎሉ ክልሎችና ማህበረሰቡ በባለቤትነት በቅንጅት መስራት አለባቸው ብለዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026