አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 9/2017 (ኢዜአ)፡-የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ የአምራች ኢንዱስትሪውን የውጭ ምንዛሪ እና የፋይናንስ አቅርቦት በማሻሻል የዘርፉን አፈፃፀም ማሳደግ ማስቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
በኢትዮጵያ ከለውጡ ወዲህ በተደረጉ ሀገራዊ የሪፎርም ሥራዎች ሁሉን አቀፍ እድገትና ብልጽግናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡
ከሃምሌ ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ ገቢራዊ የተደረገው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያው ኢኮኖሚውን በማነቃቃት ተጨባጭ ለውጦችን ማሳየት ጀምሯል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በኋላ የአምራች ኢንዱስትሪው ውጤታማነት እየተሻሻለ መጥቷል፡፡
ተዘግተው የነበሩ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ወደ ምርት በማስገባት እና የማምረት አቅማቸውን በማሳደግ አቅማቸውን እንዲያሻሽሉ ማድረግ መቻሉንም ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በፊት የአምራች ኢንዱስትሪው ትልቁ ማነቆ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደነበር አስታውሰው፤ ሪፎርሙ በቂ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በመፍጠር የተሻለ የግብዓት አቅርቦት ማግኘት እንዲችሉ አድርጓል ብለዋል፡፡
በዚህም ከሪፎርሙ በኋላ በተደረገ የጋራ ርብርብ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ከ60 በመቶ በላይ ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
መንግሥት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመቀነስ ተኪ ምርቶች ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 3 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ተኪ ምርት ተገኝቷል ብለዋል፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የተኪ ምርት ስትራቴጂው ውጤታማ እንዲሆን ያስቻለ ለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ለተለያዩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የሚውሉት የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች፣ ገመዶች እና ትራንስፎርመሮች በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
አምራች ኢንዱስትሪው ምርቶችን ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ማሳደግ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረው፥ ዘርፉ በተያዘው በጀት አመት 276 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘቱን ተናግረዋል፡፡
ይሄውም ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ18 በመቶ ብልጫ እንዳለው ጠቅሰው፤ ከሀገሪቱ አቅም አንፃር ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
መንግሥት የአምራች ኢንዱስትሪዎች የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ለመፍታት 76 በመቶ ብድር ለግሉ ዘርፍ እንዲሄድ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
የዘርፉ የማምረት አቅም በመሻሻሉ እና ተጨማሪ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኢንቨስትመንት መሳብ በመቻሉ ከፍተኛ የሥራ እድል ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለአምራች ኢንዱስትሪ ምቹ ከባቢ መፍጠሩን ገልጸው፤ ዘርፉ የሚጠበቅበትን 12 በመቶ እድገት ማሳካት የሚያስችለውን አቅም ፈጥሯል ብለዋል፡፡
መንግስት የአምራች ኢንዱስትሪውን ለማበረታታት ከሚሰጠው የታክስ እፎይታ በተጨማሪ አዲስ የኢንቨስትመንት ስትራቴጂ እየተዘጋጀ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025