የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በስራ ዕድል ፈጠራ የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት በትኩረት ይሰራል

Apr 18, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 9/2017(ኢዜአ):-በስራ ዕድል ፈጠራ የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት በትኩረት እንደሚሰራ የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ።

የሀረሪ ክልል ኢንተርፕራይዝ ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ በቀጣይ አራት ወራት በሚካሄደው የስራ እድል ፈጠራ ንቅናቄ እቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተዋል ።


በመርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ በክልሉ በስራ ዕድል ፈጠራ የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በክልሉ የሚገኙ ስራ አጥ ዜጎችን ለይቶ ስልጠናዎችን በመስጠት፤በአካባቢው ላይ ያሉ ፀጋዎችን በመጠቀም ተደራጅተው ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ሰራዎች በቀጣይ ጊዜያትም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ርብርብ ይደረጋል።

በተለይ ገበያ ላይ ተፈላጊ የሆኑ የክህሎት ስልጠናዎችን ከመስጠት ጀምሮ የዜጎችን የስራ ባህል በማሳደግ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነታቸውን በዘላቂነት ለማረጋገጥ እተሰራ እንደሚገኝ ነው የጠቆሙት።

የኢንተርፕራይዝ ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ አቶ እስማኢል ዩሱፍ በበኩላቸው፥ ዜጎች ዕራሳቸውን በኢኮኖሚ ከመቻል በዘለለ አምራች እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ትኩረት ተሰቶ አጫጭር ክህሎት መር ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን ገልፀዋል።

በቀጣይ አራት ወራት ለስራ አጥ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር 50 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ወደ ስራ መገባቱን አቶ እስሚኢል መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025