የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በባህርዳር ከተማ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የኮሪደር ልማት በከፍተኛ የአመራር አባላት ተጎበኘ

Apr 21, 2025

IDOPRESS

ባህርዳር ፤ ሚያዚያ 10/2017 (ኢዜአ)፡- በባህርዳር ከተማ በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ማምሻውን በከፍተኛ አመራር አባላት ተጎበኘ።

የኮሪደር ልማቱ አካል የሆነው የሞባይልና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን ቻርጅ ማድረግ የሚያስችለው ስማርት ፖል ተከላና የማብራት የሙከራ ትግበራ ተከናውኗል።

የአረንጓዴ ልማት፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገድና ሌሎች መዝናኛዎችን በማካተት የተገነባው የሶስት ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት የመብራቱ መጀመር የከተማዋን ድምቀት የሚጨምር መሆኑ ተመልክቷል።


ማምሻውን ልማቱን የጎበኙት በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንደላማው የሚመራ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራር አባላት ናቸው።

የከተማ አስተዳደሩ የኮሪደር ልማቱ አካል የሆነውን ከአልማ ህንጻ ፊት ለፊት ዋተር ፍሮንት የሚደርሰው የ800 ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ ሰሞኑን ማስጀመሩን በወቅቱ ዘግበናል።

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ምዕራፎች የ22 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ለማካሄድ እየሰራ እንደሚገኝ ከከተማ አስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025