ሐረር፣ ሚያዝያ 14/2017(ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የመለሱ 33 የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የሐረሪ ክልል ፕላን ኮሚሽን ገለጸ።
በሐረሪ ክልል የዘንድሮ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ርዕሰ መስተዳድሩ ኦርዲን በድሪ በተገኙበት እየተገመገመ ነው።
በግምገማው ላይ የክልሉ የፕላን ኮሚሽነር ኢብሳ ኢብራሂም የክልሉን የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል።
ኮሚሽነሩ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በዘጠኙ ወራት የገጠርና የከተማውን ማህበረሰብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የመለሱ 33 ፕሮጀክቶች ተጠናቀዋል።
አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙት መካከል የከተማው የኮሪደር ልማት፣ የመንገድ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የትምህርት እና ሌሎች ፕሮጀክቶች ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።
በተጨማሪም ለህብረተሰቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የተቋማት ዕድሳትና ግንባታ፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶች ዝርጋታዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
በክልሉ ዘንድሮ በመተግበር ላይ ከሚገኙት 27 ነባርና 57 አዳዲስ ፕሮጀክቶች መካከል ደግሞ 39ኙ ከ60 እስከ 95 በመቶ የተጠናቀቁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በቀሪ የበጀት ወራት እነዚህን በተቀናጀ መንገድ በማጠናቀቅ የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በላቀ ደረጃ ለመመለስ መረባረብ ይገባል ብለዋል።
የግምገማው መድረኩ ቀጥሎ በአሁኑ ሰዓት የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ ያህያ ክልሉ የሚያመነጨውን ያህል ገቢ ለመሰበሰብና የክልሉን ህዝብ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት ባለፉት ዘጠኝ የበጀት ወራት የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት እያቀረቡ ይገኛሉ።
የበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማውን ርዕሰ መስተዳደሩ ኦርዲን በድሪ እየመሩት ሲሆን የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የየወረዳዎቹ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ናቸው።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025