መቀሌ፤ ሚያዚያ 14/2017(ኢዜአ)፦ በትግራይ ክልል የታዳጊዎችን የቁጠባ ባህል በማሳደግ በቀጣይ የተሻለ ህይወት መምራት የሚያስችሉ አሰራሮች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑ ተገለጸ።
የክልሉ የገበሬዎች የቁጠባና ብድር የህብረት ስራ ማህበራት ታዳጊ ህጻናት የቁጠባ ልምድን እንዲያዳብሩ ከወላጆቻቸው ጋር በተደረገ ጥረት እስካሁን 38 ሚሊዮን ብር መቆጠብ እንደተቻለም ተመልክቷል።
አዲሱን ትውልድ በቁጠባ ባህል ኮትኩቶ ማሳደግ የወደፊት ህይወቱን የተሻለ እንዲሆን ዕድሉን ሊያሰፋ እንደሚችል እሙን ነው።
የታዳጊዎችን የቁጠባ ባህልን በማሳደግ በቀጣይ የተሻለ ህይወት መምራት የሚያስችሉ አሰራሮች ተግባራዊ እየተደረጉ ሲሆን በዚህም ወላጆችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት እገዛ ወሳኝ መሆኑ ይታመናል።
በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ የህብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲ ምክትል ኃላፊ አቶ የማነ ገብረመስቀል፤ የቁጠባ ባህልን ማሳደግ ለምጣኔ ሃብት እድገት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
በዚህ ረገድ በተለይም የወጣቶችና የታዳጊዎች የቁጠባ ባህል እያደገ እንዲሄድና የወደፊት ህይወታቸውን በተሻለ መልኩ መምራት እንዲችሉ መስራት ይገባል ብለዋል።
በተለያዩ አካባቢዎች የአርሶ አደሮች ልጆች ላይ ትኩረት በማድረግ እንዲቆጥቡ በማድረግ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 83 ሺህ ታዳጊዎች 38 ሚሊዮን ብር እንዲቆጥቡ ተደርጓል ነው ያሉት።
የታዳጊዎቹ የቁጠባ ልምድ ለቀጣይ ህይወታቸው ጥሩ መሰረት የሚያስይዝ መሆኑን ጠቅሰው በሁሉም አካባቢዎች ልምድ ሆኖ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ታዳጊዎቹ ከልጅነታቸው ጀምሮ የቁጠባ ባህልን ትርጉምና አስፈላጊነት እንዲገነዘቡ ተከታታይ የግንዛቤ ትምህርት የሚያስፈልጋቸው መሆኑንም አንስተዋል።
በክልሉ ከ500 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ባለፉት ዘጠኝ ወራት 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በመቆጠብ የሚያስፈልጋቸውን የግብርና ግብዓት በቀላሉ ለመግዛት መቻላቸውም ታውቋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025