የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ተወዳዳሪነት በእጅጉ የሚያጎሉ ናቸው

Apr 24, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 15/2017 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ እየተከናወኑ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በእጅጉ የሚያሳድጉ መሆናቸው ተገለጸ፡፡


የፕሮጀክቶች በፍጥነትና በጥራት መጠናቀቅ የመፈጸም አቅምን ከፍ ያደረገ ስለመሆኑም ተጠቁሟል፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትናንትናው ዕለት የካዛንችስ የኮሪደር ልማት ስራን መመረቃቸው ይታወቃል፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የከተሞቻችንን የማዘመን ሰፊ ጥረት አይነተኛ ማሳያ የሆነውን በካዛንቺስ ያለውን የኮሪደር ልማት ክፍል በይፋ መርቀናል ብለዋል፡፡


የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተጠሪ ተቋማት እና የብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የካሳንቺስ የኮሪደር ልማት ስራዎችን፣ የመልሶ ማልማት፣ የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል፣ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልና ጨምሮ ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።


በዚሁ ወቅት በሰጡት አስተያየትም የልማት ስራዎቹ የከተማዋን ዕድገት የሚያፋጥኑና የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡


በጉብኝቱ ላይ ከብሔራዊ ቤተ-መንግሥት የተሳተፉት አስቴር ምንውየለት የኮሪደር ልማት ስራዎች በፍጥነት፣ በጥራትና ሁሉንም የመሠረተ ልማቶች ባሟሉ መልኩ መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡


የካዛንቺስ የኮሪደር ልማት ስራዎች ደረጃቸውን የጠበቁ የተሽከርካሪ፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶች እንዲሁም የተቀናጀ የመሠረተ ልማትን ጨምሮ ሌሎችንም ባካተተ መልኩ የተገነባ ማራኪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


ከአፍሪካ ልህቀት አመራር አካዳሚ የተሳተፉት አለሙ ገላን በበኩላቸው ለልማት ተነሺዎች ሁሉንም ዓይነት የመሠረተ ልማት ያሟላ የመኖሪያ ቤት ጨምሮ ለኑሮ ምቹ የሆነ ከባቢ መሰጠቱ ልማቱ ህዝቡን ተጠቃሚ እያደረገ ለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡


ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተሳተፉት ሐረግ ታደሠ እንዳሉትም፤ በአዲስ አበባ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች የስራ ባህልን በመቀየር ላይ የሚገኙ እና የገጽታ ግንባታን በማሳደግ ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡


ከአፍሪካ ልህቀት አመራር አካዳሚ ብሩክ አመንቴ በበኩላቸው፥ አዲስ አበባ ለሌሎች ከተሞች ሞዴል መሆን ወደ ምትችልበት ደረጃ እየተሸጋገረች መሆኗን አንስተዋል፡፡


አዲስ አበባ በከፍተኛ የለውጥ ሂደት ላይ እንደምትገኝ የተጠናቀቁና በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ የልማት ስራዎች ማሳያ ናቸው ብለዋል፡፡


ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የጉብኝቱ ተሳታፊ ሙሉነህ ንጉሴ በሰጡት ሃሳብም፥ የፕሮጀክቶች በፍጥነትና ጥራት መጠናቀቅ ባህል እየሆነ መምጣቱን እንደሚያሳይ ተናግረዋል።


በአዲስ አበባ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡና የስራ ባህልን የቀየሩ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025