የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ በዲጂታል ዓለም ተወዳዳሪ ለመሆን በቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት ብቁ ዜጋን ለማፍራት ትኩረት ተሰጥቷል

Apr 27, 2025

IDOPRESS

አርባ ምንጭ፤ ሚያዝያ 17/2017(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዲጂታል ዓለም ተወዳዳሪ ለመሆን በቴክኖሎጂ፣ በእውቀትና በክህሎት የበቃ ዜጋን ለማፍራት በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ።

በክልሉ የመጀመሪያ ዙር ክልላዊ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድርና አውደ ርዕይ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።


የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተወካይና የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ እንደገለጹት፣ በዲጂታል ዓለም ተወዳዳሪ ለመሆን በክልሉ በቴክኖሎጂ፣ በዕውቀትና በክህሎት የበቁ ዜጎችን ለመፍጠር በትኩረት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

በክልል ደረጃ እየተካሄደ ያለው ውድድርና ዐውደ ርዕይም የተሻለ የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት ያላቸውን ዜጎች ከመለየት ባለፈ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ ቴክኖሎጂዎችን ለመቅዳት እና ለማሸጋገር ሚናው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ረገድ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ በስሩ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን እንዲያፈሩ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን አስረድተዋል።

የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዮት ደምሰ በበኩላቸው ውድድሩ በቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው፣ ሙያና ሙያተኞችን የማበረታታት ዓላማም እንዳለው ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ዜጎች የሙያ ክቡርነትን ተረድተው እንደዝንባሌያቸው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማትን እንዲቀላቀሉ ለማስቻል ነው ብለዋል።

በክልሉ በ35 የስልጠና ኮሌጆች ዜጎች በቴክኖሎጂ፣ በክህሎትና በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ሥራዎች እንዲበቁ በልዩ ትኩረት እየተሠራ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ በዛብህ ገበየሁ ናቸው።

ሰልጣኞቹ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ አሻራቸውን ሊያኖሩ ይገባል ብለዋል።

ክህሎት መር የሥራ ዕድል በመፍጠርና ለአምራች ኢንዱስትሪው የሰው ሃይል በማቅረብ በኩል አበረታች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የዘርፉ አሠልጣኞችና ሠልጣኞች እንዲሁም ኢንተርፕራይዞች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025