መቱ፤ሚያዝያ 18/2017 (ኢዜአ)፦በኢሉ አባቦር ዞን 1 ሺህ 900 ሄክታር መሬት ማልማት የሚያስችሉ አነስተኛ መስኖ ግድቦች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ መስኖ ልማት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የኢሉ አባቦር ዞን መስኖ ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ደመቁ ተረፈ እንዳሉት፥ አነስተኛ መስኖ ግድቦች ግንባታው በሁለት ወረዳዎች እየተከናወነ ነው።
የክልሉ መንግስት 'ፊና' በተሰኘ ፕሮጀክት ውኃ አጠር በሆኑ አካባቢዎች አነስተኛና መለስተኛ የመስኖ ግድቦች ግንባታ እያካሄደ ሲሆን በዞኑ በግንባታ ላይ የሚገኙ ግድቦችም የዚሁ አካል ናቸው ብለዋል።
የፕሮጀክቶቹ ግንባታ ሲጠናቀቅ የአካባቢው አርሶ አደሮችን የማምረት አቅም በማሳደግ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸው እንደሆነ ገልጸዋል።
በሁለቱ ወረዳዎች 4 ሺህ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ የሚችሉት እነዚሁ ግድቦች ግንባታቸው በ400 ሚሊዮን ብር ወጪ ነው እየተከናወነ የሚገኘው ብለዋል።
ግድቦቹ በሚገነቡበት አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮችም የመስኖ ግድቦቹ ከክረምት ባለፈ በበጋ ወራት ተጨማሪ የማምረት አቅም እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል።
አርሶ አደር አበበ ሀብተወልድ ፕሮጀክቶቹ በአካባቢያቸው የሚገኘውን ወንዝ በግብርና ስራቸው ላይ በመጠቀም ክረምትና በጋ ማምረት የሚያስችለን ነው ብለዋል።
በዚህም ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ወደስራ ሲገባ በዝናብ ወቅት ብቻ ላይ የተመሰረተውን ግብርናቸውን በማሻሻል ዓመቱን ሙሉ ማምረት እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል።
ሌላው አቶ ጫንያለው ያደታ ደግሞ የመስኖ ግድቡ በግብርና ስራ እያከናወኗቸው ባሉ የተለያዩ ኢኒሼቲቮች ላይ ያላቸው ተሳትፎ እንዲጨምር ይረዳል ብለዋል።
በአካባቢያቸው ሌሎች የግብርና ስራዎችም ላይ ጠንክረው በመስራት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እንደሚያግዛቸው አክለዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025