የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ዓላማ የኢትዮጵያን ምርት ለዓለም ማስተዋወቅ ነው - ሚኒስትር መላኩ አለበል

Apr 27, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ዓላማ የኢትዮጵያን ምርት ለዓለም ማስተዋወቅ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ።

የ2017 ዓ.ም ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው።

ውድድሩን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን፥ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ 4ኛ ዓመትን አስመልክቶ የተሰናዳ መሆኑ ተገልጿል።


የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በውድድሩ ማስጀመሪያ ላይ እንደገለጹት፥ የጎዳና ላይ ውድድሩ ዓላማ የኢትዮጵያን ምርት ለዓለም ማስተዋወቅ ነው።

አምራችና ጤናማ ትውልድ ለማፍራት ስፖርታዊ ውድድሩ ትልቅ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል።

በውድድሩ የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ክለቦችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አደባባይ በሚደምቅበት የአትሌቲክስ ስፖርት ውድድር መካሄዱ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለማስተዋወቅ ገንቢ ሚና እንዳለውም አንስተዋል።

መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ላደረገው የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር መካሄድ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ድርጅቶች፣ ግለሰቦችና ተወዳዳሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።


የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፥ ያለፉት የለውጥ ዓመታት የስፖርት ልማት ስራዎች ስፖርት ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው እያስቻሉ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ ወዲህ ከውጪ ይገቡ የነበሩ የስፖርት ትጥቅ አልባሳትን በሀገር ውስጥ በጥራት በማምረት ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በሩጫ ውድድሩ በሁለቱም ፆታዎች በቅደም ተከተል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች የ300ሺህ፣ የ200ሺህ እና የ100ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት የሚበረከትላቸው ይሆናል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በ2014 ዓ.ም ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪ ማነቆዎችን በዘላቂነት በመፍታት መዋቅራዊ ሽግግር፣ ተወዳዳሪ፣ ምቹ የቢዝነስ ከባቢያዊ ሁኔታን የመፍጠር እንዲሁም በሀገር ውስጥ ትላልቅ አምራች ኢንዱስትሪዎችን የመገንባት ዓላማን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026