የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የግብርና ሥራን የሚያዘምኑ አዳዲስ የፈጠራ ውጤቶች ላይ ትኩረት አድርገናል-በፈጠራ ሥራ የተሰማሩ ወጣቶች

May 6, 2025

IDOPRESS

ደሴ፤ ሚያዚያ 23/2017(ኢዜአ)፡-የግብርና ሥራን ጊዜና ወጪ መቆጠብ የሚያስችሉ አዳዲስ የፈጠራ ውጤቶች ላይ ትኩረት ማድረጋቸውን በፈጠራ ሥራ የተሰማሩ ወጣቶች ገለጹ።

በኮምቦልቻ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የአማራ ክልል 9ኛው የቴክኖሎጂ፣ የክህሎት፣ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር እንዲሁም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የንግድ ትርዒት እና የደረጃ ሽግግር ሳምንት ዛሬ ተጠናቋል።

የቴክኖሎጂ መዘመንና የዲጂታላይዜሽን መስፋፋትን ተከትሎ በየአካባቢው ያሉ ወጣቶች ከጊዜው ጋር የሚራመዱ የፈጠራ ውጤቶችን በማበርከት ላይ ይገኛሉ።

በተለይም የኢትዮጵያን የግብርና ሥራ በማዘመን እና ጊዜንና ወጪን በመቀነስ ምርታማነትን የሚጨምሩ ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት ላይ በርካታ ወጣቶች እየሰሩ ናቸው።

በ ንግድ ትርዒት እና የደረጃ ሽግግር ሳምንት ከተሳተፉ ወጣቶች መካከል የጎንደር ከተማ ነዋሪው ወጣት ውብሸት ታዬ የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ እና የበቆሎ መፈልፈያ ማሽን መስራቱን ይገልጻል።

የወጣቱ የፈጠራ ሥራ የእንስሳት መኖን በቀላሉ በማቀነባበር እንዲሁም በቆሎን በፍጥነት በመፈልፈል የአርሶ አደሩን ጉልበትና ጊዜ እንደሚቆጥብ ተናግሯል።

የበቆሎ መፈልፈያ ማሽኑ ጊዜን መቆጠብ የሚችልና ተረፈ ምርቱን በመጠቀም ለእንስሳት መኖ በቀላሉ የሚያቀነባብር መሆኑንም ይናገራል።


ሌላው ተሳታፊ የከሚሴ ከተማ ነዋሪው ወጣት ሰይድ አህመድ ደግሞ፤ በቀን ሁለት ሄክታር መሬት ማረስ የሚችል ማሽን በመፍጠር ይፋ አድርጓል።

እንደ ወጣቱ ገለጻ በአንድ ሰው ብቻ የሚንቀሳቀሰው ይህ ማሽን ከእርሻ ሥራ ባለፈ የውሃ መሳቢያ ሞተር ጭምር የተገጠመለት በመሆኑ ለግብርና ሥራ ጠቀሜታው የላቀ ነው።


በመሆኑም የፈጠራ ሥራውን በቴክኖሎጂ በማስደገፍና በማስፋት ለአርሶ አደሩ ተደራሽ የማድረግ ዕቅድ እንዳለው ጠቅሶ፣ ለስኬቱ ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህር ኢንጂነር አብዱልከሪም ሰይድ፤ የወጣቶቹ የፈጠራ ውጤት በተለይ ለግብርና ዘርፍ ትልቅ ተስፋ መሆኑን ተናግረዋል።

የፈጠራ ሥራዎቹ ይበልጥ ዳብረውና በብዛት ተመርተው ለአርሶ አደሮች ተደራሽ እንዲሆኑም የሁሉም ድጋፍና ትብብር ያስፈልጋል ብለዋል።


የአማራ ክልል ሥራና ስልጠና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አወቀ ዘመነ በበኩላቸው፤ የወጣቹን የፈጠራ ሥራዎች አድንቀው በስፋት ጥቅም ላይ እንዲውሉ የማገዝና የማበረታታት ሥራ ይሰራል ብለዋል።

በክልሉ 121 የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎችን በማወዳደር የተሻሉት ተለይተው በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲወዳደሩ የሚደረግ መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025