የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የቴክኖሎጂና የፈጠራ ውድድሩ የተሻለ በማምረት ተጠቃሚነትን ማሳደግ የሚያስችል ልምድና ትስስር ፈጥሮልናል - ተሳታፊዎች

May 6, 2025

IDOPRESS

ቦንጋ፤ ሚያዝያ 24/2017(ኢዜአ)፦ በውድድሩ የተሻለ በማምረት ተጠቃሚነትን ማሳደግ የሚያስችል ልምድና የገበያ ትስስር ማግኘታቸውን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የቴክኖሎጂና የፈጠራ ውድድር ተሳታፊዎች ገለጹ።

በክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ''ብሩህ አዕምሮዎች፣ በክህሎት የበቁ ዜጎች'' በሚል መሪ ሐሳብ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድርና ዐውደ ርዕይ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።


በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአግሮ ፕሮሰሲንግ መምህር ሙሉቀን መኮንን፣ በኮሌጁ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እየሰሩ እንዳሉ ገልጸዋል።

ውድድሩ ለቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ልዩ ትርጉም እንዳለው ጠቅሰው፣ በበለጠ ለማምረትና ተጠቃሚ መሆን የሚያስችል ልምድና የገበያ ትስስር የተፈጠሩበት መሆኑን ተናግረዋል።

ለውድድሩ ከወዳደቁ ቁሶች የተሰራ የፈሳሽ ሳሙና ማምረቻ ማሽን ይዘው መቅረባቸውን ጠቁመው፣ ምርቱን በዝቅተኛ ዋጋ በማቅረብ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።


የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ማሽን ይዘው ለውድድር የቀረቡት የቴፒ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መምህር በልስቲ ይታየው፣ ውድድሩ የፈጠራ ሥራቸውን አሻሽለው ለመስራት ልምድና ሀሳብ ያገኙበት መሆኑን ተናግረዋል።

በውድድሩ ይዘው የቀረቡት የመኖ ማቀነባበሪያ ማሽን ጊዜና ጉልበት ስለሚቆጥብ በእንስሳት አርባታና ማድለብ ሥራ የተሰማሩ ማህበራትና ግለሰቦችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።


የቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የኤሌክትሮ ቴክኖሎጂ የትምህርት ክፍል ሰልጣኝ አዲሱ አቢ፣ በኮሌጁ በተሰጠው ተግባር ተኮር ስልጠና ታግዞ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግሯል።

ከእነዚህ መካከል የትራፊክ እንቅስቃሴ ቁጥጥር ስራን የሚያግዝና የሚያዘምን የትራፊክ መብራት በውድድር ላይ ይዞ መቅረቡን ገልጾ፣ በውድድሩ ለቀጣይ ስራው የሚሆን ጠቃሚ ግብዓቶች ማግኘቱን ገልጿል።


የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትልና የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ኃላፊ ቤተልሔም ዳንኤል በበኩላቸው፣ በክልሉ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ቴክኖሎጂን የሚፈጥሩና የሚቀዱ ዜጎችን ለማፍራት በትኩረት እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የስልጠና አሰጣጡ የክልሉን ጸጋዎች መሰረት ያደረገና የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ ቴክኖሎጂዎች ላይ ማተኮሩን ጠቁመው በውድድሩ የቀረቡ የፈጠራ ውጤቶችም ይህንን በተጨባጭ ያሳዩ ናቸው ብለዋል።

እንደ ኃላፊዋ ገለጻ በውድድሩ ሦስት የጥናትና ምርምር፣ 14 የቴክኖሎጂ እንዲሁም 24 የክህሎት ሥራዎች ቀርበዋል።


የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አብይ አንደሞ(ዶ/ር) በሰጡት አስተያየት በክልሉ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እንዲፈጥሩና የፈጠሩትን አጠናክረው እንዲሄዱ ትኩረት ተደርጓል።

ተቋማቱ የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱና የመግዛት አቅምን ያገናዘቡ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በጥራት እያመረቱ መሆናቸውን ጠቁመው፣ የፈጠራ ውጤቶቹን ወደ ህብረተሰቡ የማሰራጨት ሥራ ይሰራል ብለዋል።

ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተካሄደ ውድድር ላይ በአሰልጣኝ መምህራንና ሰልጣኞች የተሰሩ የተለያዩ የቴክኖሎጂ፣ የፈጠራ እና የምርምር ሥራዎች ለውድድር የቀረቡ ሲሆን አሸናፊ ለሆኑት ማበረታቻ ሽልማትና ዕውቅና ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025