አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 27/2017(ኢዜአ)፦በአፍሪካ አሕጉራዊ የኢኮኖሚ ውሕደት ለመፍጠር አገራት የገበያ ዕድሎችን በማስፋት የንግድ ትስስራቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ሳምንት ሁለተኛው ተቋማዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፣ የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ዋና ፀኃፊ ቺሌስ ካፕዌ፣ ሌሎች የኮሜሳ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ዘላቂና አስተማማኝ ኢኮኖሚ መገንባት ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው።
ለአየር ንብረት የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተግባራዊ ማድረጓን ገልጸዋል፡፡
የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት አገር አቀፍ ኢኒሼቲቭ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ አሕጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናን በሙከራ ደረጃ ለመጀመር መዘጋጀትን ጨምሮ ሌሎችን ቀጣናዊና አህጉራዊ ኢኒሼቲቮችን መፈረሟን ጠቁመዋል፡፡
በቱሪዝም፣በማዕድንና በግብርና ዘርፎች ያላትን እምቅ አቅም ለመጠቀም እንደ ኮሜሳ ካሉ የጋራ ገበያዎች ጋር በትኩረት ትሰራለች ብለዋል፡፡
በአፍሪካ የኢኮኖሚ ውሕደት ለመፍጠር አገራት ያላቸውን አቅም በመጠቀምና የገበያ ዕድሎችን በማስፋት የንግድ ትስስራቸውን ማጠናከር እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኃይልና መሰረተ ልማት ማስተሳሰር ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ውህደት የበኩሏን ሚና እየተወጣች መሆኑን ገልጸው፤ በንግድ ስርዓቱ ለሚያጋጥሙ ፈተናዎችን የጋራ መፍትሔ በማበጀት ምቹ ከባቢ መፍጠር ይገባል ብለዋል፡፡
የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ዋና ፀኃፊ ቺሌስ ካፕዌ፤ ለአየር ንብረት ተፅዕኖ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት የፈጠራ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቅሰው፤ ለንግድ ሥራ ፈጣሪዎች ተገቢ ድጋፍ ሊደረግ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
በመሰረተ ልማት የተሳሰረችና የበለፀገች አፍሪካን እውን ለማድረግ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን አይነት የኢንዱስትሪ ሥራዎችን በሁሉም ዘርፎች ማስፋት ይገባል ብለዋል፡፡
የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ሴቶች ቢዝነስ ፌዴሬሽን ሰብሳቢ ማውረን ሱምቤ፥ ሴት ስራ ፈጣሪዎች ያላቸውን አቅም አውጥተው እንዲጠቀሙ ዕድሉን ማመቻቸት ይገባል ብለዋል።
ኮሜሳ ሴቶችን በቴክኖሎጂ በማብቃትና ተጠቃሚ በማድረግ ሰፊ የገበያ እድል እንዲመቻችላቸው እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ሳምንት "የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የግብርና፣ማዕድን እና ቱሪዝም የእሴት ሰንሰለቶችን በማጎልበት ክልላዊ ውህደትን ማፋጠን" በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች ይከበራል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025