የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በማምረት ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ የመገንባት ፍላጎትን ማሳካት ያስችላል - ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ

May 7, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በማምረት ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ የመገንባት ፍላጎትን ማሳካት የሚያስችል መደላድል የሚፈጥር መሆኑን ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ፡፡

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ያለውን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሚያዚያ 25 እስከ 29 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆየውን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች በመፍታት የማምረት አቅማቸው አጎልብቷል፤ በኤክስፖውም ከ288 በላይ አምራቾች እየተሳተፉበት ነው፡፡


ፕሬዚዳንት ታዬ ከጉብኝቱ በኋላ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ መንገድ ማምረትና ምርታማነትን በመጨመር ጥቅል ሀገራዊ እድገትን ማሳደግ ነው።

የአንድ ሀገር እድገት የሚመሰረተው በማምረት መሆኑን ገልጸው፤ በማምረት ላይ የተሰማሩ ሀገራት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እድገት እንደሚያሳዩ ተናግረዋል፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪውን የማምረት አቅም በማሳደግ የሥራ እድል የሚፈጥርና ነገ የተሻለ ለማምረት መሰረት የሚጥል መሆኑን ገልጸዋል።


የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በማምረት ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ ለመገንባት የምናስበውን እውን ማድረግ የሚያስችል መደላድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ታምርት መርሐ ግብር ዘርፉን በማነቃቃት በዜጎች ዘንድ የእንችላለን መንፈስን ያላበሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኤክስፖው ኢትዮጵያ የማምረት አቅም እንዳላት የሚያሳይ ነው፤ በተስፋ እንድንናፍቅ የሚያደርጉ ምርቶች የቀረቡበት ነው ብለዋል፡፡

በኤክስፖው ከቆዳ የተሰሩ የተለያዩ ምርቶች በዓለም አቀፍ የጥራት መመዘኛ መስፈርት ደረጃቸውን ያሟሉ መሆናቸውን ተመልክቻለሁ ብለዋል።


በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶች የቀረቡበት መሆኑን ገልጸው፤ ምርቶቹን የኢትዮጵያን መቻል የሚገልጡ፤ የሰዎችን ብልህነት የሚያሳዩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ በራስ ምርት የመኩራት ባህል ዝቅተኛ መሆኑን ገልጸው፤ ይህንን የተሳሳተ ምልከታ ማስወገድ ይገባል ብለዋል፡፡

የዓለም ገበያ ሰፊ፣ ሸማቹ በርካታ መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ መሰረታዊው ጉዳይ የምርት ጥራት መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ምርቶች ብዙ የሚያስኬዱ ለእኛ ዓይን ከፋች፣ በዓለም ገበያ መስፋፋት የሚችሉ መሆናቸውምን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025