ሐረር፤ ሚያዝያ 29/2017(ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል ለአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየተዘጋጁ መሆኑ ተገልጿል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ሮዛ ዑመር በክልሉ የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ዝግጅትን አስመልክተው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በክልሉ ለመጪው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ላላቸው የችግኝ ዓይነቶች ትኩረት ተሰጥቷል።
በዚህም በዘንድሮው ክረምት ከሚተከሉ ችግኞች ውስጥ 70 በመቶው ለምግብነት የሚያገለግሉ የፍራፍሬና አትክልት ችግኞች ሲሆኑ 30 በመቶዎቹ ደግሞ የደን ችግኞች ናቸው ብለዋል።
በተለይም በክልሉ የሚታወቁና በአሁኑ ወቅት እየጠፉና በመጥፋት ላይ የሚገኙ እንደ አምባሾክ፣ ጊሽጣና ሌሎች ችግኞችን የማዘጋጀት ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ እንደሚገኝም አክለዋል።
ይህም የህብረተሰቡን ፍላጎት ታሳቢ በማድረግና የፍራፍሬ ዝርያዎችን ወደ ቀድሞ ሁኔታ ለመመለስ በማሰብ ተግባራዊ የተደረገ ነው ብለዋል።
በክልሉ በሚገኙ ሶስት የችግኝ ማዘጋጃ ጣቢያዎች ላይ ችግኝ የማዘጋጀቱ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ የተፈጥሮ ሃብት ዳይሬክተር አቶ አራርሶ አደም ናቸው።
ለተከላ የሚሆን ስፍራ የመለየት እና የማዘጋጀት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝና በዚህም ዘንድሮ በክልሉ በተለያዩ ስፍራዎች 1 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ችግኝ እንደሚተከል ተናግረዋል።
ባለፈው ክረምት በክልሉ በአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር በተራቆቱ አካባቢዎች የተተከሉት ችግኞች በሚደረግላቸው እንክብካቤ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም አመልክተዋል።
በክልሉ የጠፉና እየጠፉ የሚገኙ የፍራፍሬና የሐረር ቡና ችግኝን የማዘጋጀት ስራ ማጠናቀቃቸውንና የደንና የመኖ ችግኞችን እያዘጋጁ እንደሚገኙ የተናገሩት ደግሞ በቢሮው የችግኝ ጣቢያዎች ስራ ክትትልና ድጋፍ ባለሙያ አቶ ሻሜ ደሴ ናቸው።
የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራ አካባቢን ወደ ለምለምነት ከመቀየር ባለፈ ለእኛም የስራ እድል ፈጥሮልናል፤ ችግኞቹም በወቅቱ እንዲደርሱ እያዘጋጀን እንገኛለን ያሉት የችግኝ ጣቢያ ሰራተኛ የሆኑት ወይዘሮ ዘምዘም አብዱራህማን ናቸው።
የችግኝ ዝግጅት ስራውን እያከናወኑ መሆኑን የተናገረችው ደግሞ ሌላዋ የችግኝ ጣቢያ ሰራተኛ ሰሚራ መሐመድ ናት።
በተለይ እንደ ከዚህ በፊቱ ከችግኝ ማዘጋጀቱ ጎን ለጎን በተከላው ስራ እንደምትሳተፍም ጨምራ ተናግራለች።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025