የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር ተፈጽሟል-ሚኒስትር መላኩ አለበል

May 8, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 29/2017 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር መፈጠሩን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ።


የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በሦስተኛው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ማጠቃለያ መርሐግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ማምረት የህልውና አጀንዳ ነው ብለዋል።


ሀገር አቀፍ የ2017 የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከመካሄዱ አስቀድሞ በክልሎች፣ በዞኖችና በወረዳዎች 168 የውይይት መድረኮች እና 94 የንግድ ትርኢቶች መካሄዳቸውን ገልጸው፤ በነዚህ የንግድ ትርኢቶቹ 400 ሚሊዮን ብር የሚገመት ግብይት መፈፀምንም ጠቅሰዋል።


ማምረት የህልውና አጀንዳ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ የሀገር ውስጥ ምርትን ማስፋትና የመጠቀም ባህልን ለማሳደግ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በተከታታይ እየተካሄደ ነው ብለዋል።


የኢትዮጵያ ታምርት የ2017 ኤክስፖ በርካታ አምራቾች ምርቶቻችን እንዳቀረቡበትና ከ120 ሺህ በላይ ጎብኝዎች እንደተሳተፉበትም ገልጸዋል።


በኤክስፖው ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ግብይትና ገበያ ትስስር መፈጸሙን ጠቅሰው፥ የዘርፉን ማነቆዎች ለመፍታት የሚያስችሉ የፓናል ውይይቶች እንደተካሄዱም አንስተዋል።


በኤክስፖው በምርት ብዛ፣ አይነትና በመጠን ከፍተኛ እድገት ተመዝግቧል ያሉት ሚኒስትሩ፥ የሀገር የፈጠራ አቅም የታየበት መድረክ መሆኑንም ተናግረዋል።


ኢትዮጵያ ከማሸለብ ዘመን ወጥታ በዕድገት ጎዳና እንድትጓዝ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑንም ገልጸዋል።


ንቅናቄው የገጠር ኢንዱስትሪን ለመጀመር የሚያስችል ዕድል መፍጠሩን በማንሳት፥ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በመጪዎቹ ዓመታትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።


በቀጣይ ዓመትም ከሚያዚያ 24 እስከ 28/2018 ዓ.ም ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025