የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ዩኒቨርሲቲው የሀገር የትኩረት አቅጣጫዎችና የቴክኖሎጂ ፈጠራና ሽግግር ላይ በትኩረት እየሰራ ነው 

May 12, 2025

IDOPRESS

ወልቂጤ፤ ግንቦት 3/2017(ኢዜአ)፦ የሀገር የትኩረት አቅጣጫዎች እንዲሁም የቴክኖሎጂ ፈጠራና ሽግግር ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ገለጸ።

የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ ተግባር ተኮር የጥናትና ምርምር ሥራዎች ላይም እንዲሁ በማተኮር ውጤታማ ሥራ እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል።

በዩኒቨርሲቲው 6ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ "እውቀት መር ኢኮኖሚ ለድህነት ቅነሳና ለማህበራዊ ዋስትና'' በሚል መሪ ሀሳብ ተካሂዷል።


የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፋሪስ ደሊል(ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራው ጎን ለጎን የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግሮች የሚፈቱ ተግባር ተኮር የምርምርና ጥናት ሥራዎችን ያከናውናል።

በተለይም የህብረተሰቡን ኑሮ የሚያሻሽሉ የግብርና፣ ትምህርትና ጤና ዘርፍ ውጤታማና ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጡ የጥናትና ምርምር ስራዎች በማከናወን ተግባር ላይ እንዲወሉ ለሚመለከተው አካል ማቅረቡን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የሀገር የትኩረት አቅጣጫዎች እንዲሁም የቴክኖሎጂ ፈጠራና ሽግግር ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው በቴክኖሎጂና ፈጠራ ዘርፍ የእንሰት መፋቂያ ማሽን ሰርቶ በማህበር ለተደራጁ ወጣቶች ሽግግር ማድረጉን ገልጸው፣ ማሽኑ የእናቶችን ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ ቆጥቧል ብለዋል።


ከጥናት ባለፈ ወደ ተግባር የተቀየሩ 19 የምርምር ውጤቶች እና 57 ፕሮጀክቶች ወደ ማህበረሰቡ ተደራሽ መደረጋቸውን የገለፁት ደግሞ የዩኒቨርስቲው የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ዮሐንስ ገብሩ(ዶ/ር) ናቸው።

በእንስሳት ዝርያ ማሻሻልና በአሳ ልማት ዘርፍ የተለያዩ ጥናቶችን ከማድረግ ባሻገር ወደ ተግባር በመቀየር ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑንም ጠቅስዋል።

ከኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች መካከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ተጠባባቂ ዲንና የኢኮኖሚክስ መምህሩ አጥናፉ ገብረመስቀል(ዶ/ር) እንዳሉት የጥናትና ምርምር ሥራዎች ለድህነት ቅነሳና ቀጣይነት ላለው የሀገር እድገት ሚናቸው የጎላ ነው።

ለእድገት ጠቀሜታ ያላቸውን ሀገር በቀል እውቀቶች ለኢኮኖሚ ግንባታ ለመጠቀምና ለማሸጋገር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባም ገልጸዋል።

የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም በጤና ላይ የሚከናወኑ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ተግባር ተኮር መሆን እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

በኮንፍረንሱ 26 የጥናትና ምርምር ሥራዎች የቀረቡ ሲሆን ወደ ተግባር የተቀየሩ የምርምር ውጤቶችም ተጎብኝተዋል።

ለሦስት ቀናት በተካሄደው የምርምር ኮንፍረንስ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ተቋም ዳይሬክተር አክመል መሐመድ(ዶ/ር)፣ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ጥናት አቅራቢዎች እና የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና መምህራን ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025