
ወልቂጤ፤ግንቦት 2/2017(ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የም ዞን ከ87 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የኮሾ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት መብቃቱ ተገለፀ።
ፕሮጀክቱን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማእረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትራንስፖርት እና መንገድ ቢሮ ኃላፊ መሀመድ ኑርዬ (ዶ/ር ) በይፋ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
የመስኖ ፕሮጀክቱ የአርሶ አደሮችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በማሳደግና ገበያ በማረጋጋት ረገድ ያለው ፋይዳ ከፍ ያለ መሆኑም ተገልጿል።
በክልሉ የመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ካሳዬ ተክሌ፥ የመስኖ ፕሮጀክቱ ግንባታ በሳጃ ዙሪያ ወረዳ ዲቻ ቀበሌ በ2016 ዓ/ም አጋማሽ እንደተጀመረ ገልፀዋል።
በ87 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክቱ 600 የቤተሰብ መሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልፀው፥ ለእንስሳት የመጠጥ ውሃ የሚሆን ቦታ ተካቶበት መገንባቱን ተናግረዋል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይም የክልሉና የዞኑ አመራር አባላት እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026