የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በአማራ ክልል ተኪ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በማምረት አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል

May 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2017(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ተኪ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በማምረት በኩል አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ተፈሪ ታረቀኝ ለኢዜአ እንዳሉት፥ በክልሉ ለኢንዱስትሪ ምርታማነት አቅም የሚሆን የማዕድንና የግብርና ምርት የግብዓት አቅርቦት በስፋት አለ።

በበጀት ዓመቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የክልሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ከሀገር ውስጥ ባለፈ ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለውጭ ገበያ ማቅረብ የቻሉበትን ስኬታማ አፈፃፀም ማስመዝገባቸውንም ተናግረዋል።

በዚህም 48 አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ማስገኘታቸውን አስታውቀዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪ ምርታማነት አቅሞችን በማሳደግ የሀገር ውስጥ ገበያ ፍላጎትን በራስ ምርት የመተካት ስራ ቁልፍ ተግባር መሆኑንም አንስተዋል።

በዚህም በክልሉ የኢንዱስትሪ ምርታማነት አቅሞችን በማጎልበት 630 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጣ የተኪ ምርት ስራ መሰራቱን አስረድተዋል።

በዘጠኝ ወራት ውስጥ 143 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቁመው፤ በሂደቱም ከ52 ሺህ በላይ ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄም የአሰራር ችግሮችን በመፍታትና አዳዲስ ኢንቨስትመንትን በመሳብ የክልሉን የኢንዱስትሪ ልማት እያነቃቃ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በዚህም በተኪና ወጪ ንግድ ምርት በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በማምረት እምርታዊ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በ2014 ዓ.ም ከተጀመረ አንስቶም ከ485 በላይ ኢንዱስትሪዎች በአዲስ መልክ ወደ ስራ በማስገባትበርካታ የአሰራር ማነቆዎችን ማስወገድ እንደተቻለም አስረድተዋል።

የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ባለሃብቶችም መዋዕለ ነዋያቸውን ፈሰስ በማድረግ በአማራ ክልል ያለው ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025