ሰቆጣ፤ ግንቦት 6/2017(ኢዜአ)፡- ለአካባቢው የሚስማሙ የሰብል ዝርያ ለይተው ለአርሶ አደሩ በማመቻቸትና የኩታ ገጠም አሰራርን እያበረታቱ ምርታማነትን ለማሳደግ ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠላቸውን በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ የግብርና ባለሙያዎች ተናገሩ።
በቅርቡም በቀበሌና በመንደር ደረጃ የአካባቢን ስነ ምህዳር መሰረት ያደረገ የሰብል ልማት የተግባር ተኮር ስልጠና ለግብርና ባለሙያዎችና አርሶ አደሮች መሰጠቱ ተመልክቷል።
ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል በሰቆጣ ወረዳ የ02 ቀበሌ ግብርና ባለሙያ አቶ ቢራራ መለሰ በሰጡት አስተያየት ፤ በመጪው መኽር ሰብል ልማት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ለአካባቢው የሚስማሙ የሰብል ዝርያዎችን በመለየት፣ የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ማዳበሪያን በማቅረብና በኩታ ገጠም የመዝራት ዘዴን እያበረታቱ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚሁ ወረዳ የ020 ቀበሌ የግብርና ባለሙያ አቶ ባዬ መሰለ በበኩላቸው፤ በቅርቡ የተሰጠን ስልጠና የአካባበያችን ጸጋ አውቀን ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል ነው ብለዋል።
ይህንን ውደ ተግባር በማሸጋገር ለአርሶ አደሩ የሚሰጡትን ሙያዊ ድገፍ ይበልጥ አጠናክረው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ አበክረው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
በስልጠናው ከተሳታፉ የሰቆጣ ወረዳ 02 ቀበሌ ነዋሪዎች ውስጥ አርሶ አደር ማሞ መለሰ፤ የሰብል ልማታቸውን አስፋፍተው ምርታማነት ለማሳደግ ከስልጠናው የተሻለ እውቀትና ልምድ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ስልጠናው ለአካባቢያቸው ተስማሚ የሆኑ የሰብል ዓይነቶችን ለይተን እንድናለማ የሚያስችል ነው ብለዋል።
አርሶ አደር ሲሳይ አያልነህ በበኩላቸው፤ ምርታማነትን ለማሳደግ የተፈጥሮና የሰው ሰራሽ ማዳበሪያ አጠቃቀም ስልት በአግባቡ መረዳት የቻልንበት ስልጠና ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ይህንን በመጠቀም በመጪው የመኽር ወቅት ሰብልን በኩታ ገጠም ለማልማት ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።
የብሔረሰብ አስተዳደሩ ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ አዲስ ወልዴ ለኢዜአ እንደገለጹት ፤ በ2017/2018 የምርት ዘመን ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት ለመላቀቅ ትኩረት ተሰጥቷል።
በዚህም በመኸሩ ወቅት 120 ሺህ 638 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን አስታውቀዋል።
እስካሁን በሄክታር ከ7 ኩንታል የነበረውን ምርታማነት ወደ 13 ኩንታል ለማሳደግ ግብ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ይህም በምግብ ራስን ለመቻል፣ ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑና ለወጭ ንግድ የሚውሉ ገበያ ተኮር ሰብል ልማት ላይ በማተኮር ጭምር እንደሆነ ተናግረዋል።
ለዚህም ስኬታማነት ግብአት በወቅቱ በማቅረብና አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን በመተግበር ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
በቅርቡም በቀበሌና በመንደር ደረጃ የአካባቢን ስነ ምህዳር መሰረት ያደረገ የሰብል ልማት የተግባር ተኮር ስልጠና ለግብርና ባለሙያዎችና አርሶ አደሮች መሰጠቱንም አውስተዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025