የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር የተቀናጀ የግብርና ልማት ሥራ ማከናወናችን ተጠቃሚነታችንን አሳድጎታል - አርሶ አደሮች

May 15, 2025

IDOPRESS

ዲላ፤ ግንቦት 6/2017(ኢዜአ)፦ በሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር የተቀናጀ የግብርና ልማት ሥራ ማከናወናቸው ተጠቃሚነታቸውን እያሳደገው መሆኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ ዞን አርሶ አደሮች ገለጹ።

በክልሉ በየአካባቢው ያለውን ጸጋና ሃብት ታሳቢ ያደረገ የሌማት ትሩፋት ትግበራን በማጠናከር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ መቻሉም ተመላክቷል።

በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ የሚኖሩት አርሶ አደር ቦጋለ ዊሲ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በአካባቢያቸው ካሉ 20 አርሶ አደሮች ጋር ተቀናጅተው "ላክቻ" የተሰኘ የማር መንደር መስርተው ወደ ምርት ገብተዋል።

በመንደሩ 551 ዘመናዊና ባህላዊ የንብ ቀፎዎች እንዳሉና በማር ምርት ውጤታማ መሆናቸውን አንስተዋል።

በተለይ ንቦች በአካባቢው እንዲቀስሙ የተሻሻሉ የቡና ዝሪያዎችን ጎን ለጎን በማልማት የተቀናጀ የግብርና ልማት ሥራ እያከናወኑ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

በዚህም የቡና ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ አርሶ አደሮቹ በዓመት 30 ኪሎ ግራም የተጣራ ማር ለገበያ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል።

የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር የተሰማሩበትን የንብ ማነብ ሥራን ለማጠናከር እንዳስቻላቸው ገልጸው፣ በልማቱ ውጤታማ እንዲሆኑ መንግስት በተለያየ መንገድ እያደረገላቸው ያለው ድጋፍ እንዲጠናከር ጠይቀዋል።

የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን በሀገር በቀል የጥላ ዛፎች ውስጥ ማልማታቸው ለማር ምርት የሚሆን የእጽዋት ስብጥር እንደፈጠረላቸው የገለጹት ደግሞ ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ መስከረም ዳዬ ናቸው።

በዘመናዊ የንብ ቀፎዎች ታግዘው እያከናወኑት ባለው የንብ ማነብ ሥራ ከቤተሰብ ፍጆታ ባለፈ ጥራቱን የጠበቀ ማር ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በዞኑ የቡሌ ከተማ ነዋሪ አርሶ አደር ዳዊት ተፈራ በበኩላቸው የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር የተቀናጀ የግብርና ልማት በማከናወን ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እያገዛቸው መሆኑንም ተናግረዋል።

በዘርፉ በመንግስት የግብዓትና የሙያ ድጋፍ ማግኘታቸውን ጠቁመው በወተት፣ በንብ ማነብና በበግ እርባታ ሥራ መሰማራታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ሲያከናውኑት የነበረው የንብ ማነብ ሥራ ወደ ዘመናዊ የንብ ማነብ ሥራ መተካት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።

የተቀናጀ የግብርና ሥራ ማከናወናቸው ንቦች የሚቀስሙትን በቅርበት እንዲያገኙ በማድረግ የማር ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ የእንስሳት መኖ በተሻለ ሁኔታ ማግኘታቸውን ጠቁመዋል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትልና የእንስሳት ዝርያና መኖ ልማት ዘርፍ ሃላፊ አባይነህ ከዳ(ዶ/ር) በክልሉ የየአካባቢውን ጸጋና ሃብት ታሳቢ ያደረገ የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር እየተከናወነ መሆኑንና በዚህም የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።

በተለይ የማር፣ የዶሮ፣ የሥጋና የወተት መንደሮችን ከመመስረት ባለፈ ጌዴኦን ጨምሮ የጥምር ግብርና ባለባቸው ዞኖች አርሶ አደሩ በንብ ማነብ ሥራ በስፋት እንዲሳተፍ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።

ባለፉት አስር ወራት ብቻ ከ151ሺህ 400 በላይ ዘመናዊና ባህላዊ የንብ ቀፎዎች ለአርሶ አደሩ ተሰራጭተዋል ብለዋል።

በዚህ ጊዜ ውስጥም ከ14ሺህ 500 ቶን በላይ የማር ምርት ለገበያ መቅረቡን ተናግረዋል።

ይህም አምና በዓመቱ ከተገኘው የማር ምርት ብልጫ እንዳለው ጠቅሰው በወተት፣ በዶሮ ሥጋ ምርቶችም ተጨባጭ ውጤት እየተገኘ መምጣቱን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025