የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በጋምቤላ ክልል ያሉትን የተፈጥሮ ጸጋዎች አልምቶ ለመጠቀም የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ይጠናከራሉ - ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን(ዶ/ር)

May 15, 2025

IDOPRESS

ጋምቤላ፤ ግንቦት 6/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ያሉትን የተፈጥሮ ጸጋዎች አልምቶ ለመጠቀም የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን(ዶ/ር) ገለጹ።

"የክልሉ የገጠር መንገድ ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና" የተሰኘ ፕሮጀክት ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ የክልሉን የተፈጥሮ ጸጋዎች በአግባቡ አልምቶ ለመጠቀምና የተጀመረውን የልማት ስራዎችን ለማፋጠን የመንገድ መሰረተ ልማት ወሳኝ ነው።

በክልሉ ሰፊ ለም መሬት፣ ውሃ፣ ማዕድን፣ የቱሪዝም መዳረሻዎችና ሌሎች የተፈጥሮ ጸጋዎች እንዳሉ ጠቅሰው፤ እነዚህ ሀብቶች በተገቢው ለምተው ለህዝቡ ጥቅም ሳይውል እንዲቆይ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ የመንገድ መሰረተ ልማት ክፈተት እንደሆነ አውስተዋል።


ሆኖም ባለፉት የለውጥ ዓመታት በክልሉ የመንግድ መሰረተ ልማት ችግሮች ለማቃለል በክልሉና በፌዴራል መንግስት በተደረገው ጥረት ውጤቶች መታየታቸውን ገልጸዋል።

የክልሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ስራዎችን ስኬታማ ለማድረግ የተጀመሩትን የመንገድ መስረተ ልማት ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።

በተለይም ይፋ የተደረገው የገጠር መንገድ ትስስርና ተደራሽነት ፕሮጀክት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ከተረጂነት ለመውጣት ለታለመው ግብ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር እንዲሰሩ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።


የክልሉ ገጠር መንገዶች ዋና ዳይሬክተር ኮማንዳር ኡማን ኡጋላ በበኩላቸው፤ መንገድ ለሁሉም የልማት ዘርፎች መሳለጥ ዓይነተኛ ድርሻ ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይ አምስት ዓመታት የሚተገበረው ይኸው የገጠር መንገድ ትስስርና ተደረሽነት ፕሮጀክት ድልድዮችን ጨምሮ የገጠር አገናኝ መንገዶች ግንባታና ጥገና ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ይሆናል ብለዋል።

ይህም ለአርሶ አደሩ የምርት ግብዓቶችን ለማቅረብና ምርቱን ወደ ገበያ ለማድረስ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026