ደብረብርሃን ፤ግንቦት 6/2017 (ኢዜአ)፡- በመጪው የመኸር ወቅት የምግብ ዋስትናችንን ከማረጋገጥ ባሻገር ለገበያ የሚሆን ምርት ለማምረት ከወዲሁ እየሰራን ነው ሲሉ በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ አርሶ አደሮች ገለጹ።
የዞኑ ግብርና መምሪያ በበኩሉ በ2017/18 ምርት ዘመን መኸር ወቅት በሰብል ከሚለማው መሬት 20 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰበሰብ አቅዶ እየሰራ መሆኑን አመላክቷል።
በዞኑ ባሶና ወራና ወረዳ የጊፍት ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ንጉሱ አጥላው ለኢዜአ እንደገለጹት በመጪው ክረምት መኽር ወቅት በአንድ ሄክታር ከሩብ መሬታቸው ላይ ስንዴ፣ ጤፍና ባቄላ ለመዝራት ወስነዋል።
መሬታቸውን እስከ ሶስት ጊዜ ደጋግመው በማረስና ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራሳቸውን ከመቻል ባለፈ ለገበያ የሚሆን ምርት ለማምረት ከወዲሁ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የምርት ማሳደጊያ ማዳበሪያና ምርጥ ዘርን በመጠቀም ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እየሰሩ መሆኑን አስረድተዋል።
ሌላዋ አርሶ አደር ትርንጎ ግርማ በበኩላቸው በምርት ወቅቱ ግማሽ ሄክታር ማሳቸውን በስንዴና ጤፍ ዘር ለመሸፈን መሬታቸውን ደጋግመው በማረስ ለዘር ማዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
የዘንድሮ የማዳበሪያ አቅርቦት ቀደም ብሎ በመከናወኑ በእርሻ ስራቸው ላይ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ጠቁመው የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ ያለፈ ለገበያ የሚሆን ምርት ለማምረት ከወዲሁ ከማሳ ዝግጅት ጀምሮ እየተጉ መሆኑን ተናግረዋል።
በሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ አበበ ጌታቸው በበኩላቸው በመጪው የመኸር ወቅት 556 ሺህ 800 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች በዘር ለመሸፈን እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
እስካሁን በተደረገው ጥረት 449 ሺህ 157 ሄክታር መሬት በድግግሞሽ ታርሶ ለዘር ዝግጁ መሆኑን ጠቁመው ከዚህ ውስጥ 43 ሺህ 385 ሄክታር መሬት በትራክተር የታረሰ መሆኑን አመልክተዋል።
በእቅድ ከተያዘው ከግማሽ በላይ የሚሆነው መሬት በኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴና ሌሎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና አሰራሮችን በመጠቀም እንደሚከናወን አስረድተዋል።
"በአሲድ የተጠቃውን መሬት በኖራ በማከምና ዘመናዊ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በመጠቀም በመጪው መኸር 20 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰበሰብ ግብ ተይዞ እየተሰራ ነው" ብለዋል።
በመኸር ወቅቱ አርሶ አደሩ በምግብ ራስን ከመቻል ባሻገር ለኢንዱስትሪ ግብዓትና፣ ለወጪ ንግድ የሚሆኑ ምርቶች ላይ እንዲያተኩር እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025