የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የፕሮጀክቶች ግንባታ በጥራት፣ በፍጥነት እና በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የክትትልና ቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል - ባለስልጣኑ

May 15, 2025

IDOPRESS

ድሬዳዋ፤ ግንቦት 6/2017(ኢዜአ)፦ የፕሮጀክቶች ግንባታ በጥራት፣ በፍጥነት እና በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የክትትልና ቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ገለጸ።

የባለስልጣኑ አመራሮች እና ባለሙያዎች በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እየተገነቡ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲውን የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል፣ የመምህራን መኖሪያ ህንፃዎች እና በዋና ጊቢው እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በሰነድና በመስክ ገምግመዋል።

የባለስልጣኑ የቁጥጥር ዘርፍ ኃላፊ ደረጀ አረጋኸኝ፤ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የግንባታ ፕሮጀክቶች በጥራት፣ በፍጥነት እና በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በዚሁ ረገድ ተቋሙ በመላው ሀገሪቱ የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች በጥራት፣ በፍጥነት እና በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የክትትልና ቁጥጥር ሥራ እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በጥሩ ሂደት ላይ መሆናቸውን አስተውለናል ያሉት ኃላፊው በተለይም የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታሉን እንዲሁም የመምህራን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በዚህ ዓመት ማጠናቀቅ የሚያስችል ደረጃ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ለፕሮጀክቶቹ በጥራትና በተለያዘላቸው ጊዜ መጠናቀቅ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ክትትል ድጋፍና ቁጥጥር እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።

ባለስልጣኑ በቀጣይ ጊዚያት በፕሮጀክቶች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን አስቀድሞ መፍታት የሚያስችሉ ሳይንሳዊ ጥናቶች አስጠንቶ ወደ ስራ እንደሚያስገባም ጠቁመዋል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንትፊክ ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ገደፋይ(ዶ/ር) በበኩላቸው በዩኒቨርስቲው እየተከናወኑ የሚገኙ የግንባታ ፕሮጀክቶች በፍጥነት እና በጥራት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች በአካል በመገኘት የሚያደርጉት ክትትልና ድጋፍ ለፕሮጀክቶቹ መፋጠን ወሳኝ ሚና ማበርከቱንም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025