
ቴፒ፤ግንቦት 7/2017 (ኢዜአ)፦በቴፒ ከተማ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ከ5 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር በላይ የኮሪደር ልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስተዳደሩ አስታወቀ።
የከተማዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው፥ ለልማቱ ስኬታማነት የበኩላቸውን ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የቴፒ ከተማ ከንቲባ አቶ ወንድሙ ግርማ እንደገለጹት፥በከተማዋ በመጀመሪያ ዙር በአስተዳደሩና በነዋሪዎች ተሳትፎ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ በሚበልጥ ወጪ ከ5 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር በላይ ኮሪደር ለማልማት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።
ልማቱ የእግረኛ መንገድ፣ የመንገድ አካፋይ፣መናፈሻ፣ ፏፏቴና የመንገድ ዳር መብራቶች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑንና ስራውም እየተፋጠነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
በከተማዋ የኮሪደር ልማቱ ወደስራ የገባው ከህብረተሰቡ ጋር መግባባት ላይ ከተደረሰ በኋላ መሆኑን ያነሱት ከንቲባው፥ የከተማዋ ነዋሪዎች ንብረታቸውን ከማንሳት ጀምሮ በተለያየ መንገድ ድጋፍና ትብብር እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል መምህር ሰሎሞን ይትባረክ፣ በከተማዋ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ ለከተማዋ ውበት ከመሆኑ ባለፈ እድገቷን እንደሚያፋጥነው ተናግረዋል።
የኮሪደር ልማት ሥራው እንዲፋጠን ከአስተዳደሩ ጋር በመቀናጀት በገንዘብ፣በሀሳብና በጉልበት የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑንም ገልጸዋል።
የተለያዩ ከተሞችን የኮሪደር ልማት ሥራ እንደተመለከቱና ወደ ቴፒ ከተማም ልማቱ እንዲመጣ ሲመኙ እንደነበር የተናገሩት ደግሞ አቶ ጌታቸው ደለለኝ የተባሉ ነዋሪ ናቸው።
ከኮሪደር ልማቱ ባሻገር የአስፋልት መንገድ በከተማዋ መጀመሩ ለዕድገቷ ተጨማሪ እድል ይዞ ይመጣል ያሉት ደግሞ አቶ ታከለ ዘውዴ የተባሉ ነዋሪ ናቸው።
የልማት ሥራ በመንግስት ብቻ የሚከናወን እንዳልሆነ ገልጸው፥ ለኮሪደር ልማቱ ስኬታማነቱ የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በኮሪደር ልማቱ የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው የከተማዋ ወጣቶች መካከል ኢሳይያስ ቆጭቶ ነገ የተሻለች ከተማ የማየት ተስፋ ይዞ እየሠራ መሆኑን ተናግሯል።
እየተፋጠነ ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ ሲጠናቀቅ የከተማዋን ገጽታ ይቀይራል የሚል እምት እንዳለው ገልጾ፥ በልማቱ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እየሆነ መምጣቱንም ተናግሯል።
የቴፒ ከተማ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከአራቱ ብዝኃ ዋና ከተሞች አንዷ ናት።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026