የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት ምህዳርን የሚያጠናክሩ ቁልፍ የዲጅታል መሰረተ ልማቶችን ገንብታለች

May 19, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ግንቦት 8/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት ምህዳርን የሚያጠናክሩ ቁልፍ የዲጅታል መሰረተ ልማቶችን መገንባቷን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ ገለጹ።


በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በይፋ ተከፍቷል።


የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ በዚሁ ወቅት፥ቴክኖሎጂ የሁሉ ነገር መሰረት እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።


ኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታውን በቅጡ በመገንዘብና ቴክኖሎጂ ለሀገር ሁለንተናዊ ልማት ያለውን ፋይዳ በመረዳት ዲጂታል መሰረተ ልማትን እያስፋፋች ነው ብለዋል።


ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ፣የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ የሥልጠና ኢኒሼቲቭ እንዲሁም የመንግሥት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል የማስገባት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም አንስተዋል።


የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ቁልፍ የዲጂታል መሰረተ ልማቶች መገንባታቸውን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ፥ በስማርት ሲቲ ግንባታም ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ የሚሆኑ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።


አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባትና አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን ቴክኖሎጂ የማይተካ ሚና እንዳለውና ይህን የበለጠ ማሳደግ ላይ በትኩረት እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።


የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የሳይበር ደህንነት ካውንስል ሊቀመንበር መሃመድ አልኩዋቲ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ቴክኖሎጂ ዓለምን የመቀየር ትልቅ አቅም እንዳለው አንስተዋል።


የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ የብሄራዊ ደህንነትን ሉዓላዊነት ማረጋገጥ መሆኑን ጠቅሰው፥ በዚህ ላይ ሀገራት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።


ከቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የሳይበር ደህንነት ስጋቶችን ለመቀነስ ትብብርን ማጠናከርና ተለዋዋጭ የሳይበር ደህንነት ስጋትን ታሳቢ ያደረገ አቅም መገንባት ወሳኝ እንደሆነም ጠቁመዋል።


የቴክኖሎጂ ኤክስፖው እስከ ግንቦት 10/2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን የበርካታ ሀገራት ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችና ከአስር ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እየተሳተፉበት ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025