አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018(ኢዜአ)፦በሀገር በቀል ፈጠራ የተቃኘ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በአፍሪካ ለሚስተዋሉ ዘርፍ ተሻጋሪ ችግሮች ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) “አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስን ለአፍሪካ ብልጽግና እና ትብብር” በሚል ጭብጥ እየተካሄደ ባለው “አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለአፍሪካ” መርሃ-ግብር በመገኘት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለአፍሪካ የምርጫ ጉዳይ እንዳልሆነ አስረድተዋል።
በአፍሪካ የሚስተዋሉ ዘርፍ ተሻጋሪ ችግሮችን ትርጉም ባለው መልኩ ማቃለል የሚቻለው በሀገር በቀል ፈጠራ በተቃኘ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አካባቢን፣ ማህበረሰብንና ዘርፎችን የሚሻገር የለውጥ ሞተር መሆኑን ጠቅሰው፤ አህጉሪቱን እየፈተኑ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ሁነኛ አማራጭ መሆኑንም አብራርተዋል።
አፍሪካም ዘርፉን በተመለከተ አካታችነትንና የክህሎት ልማትን የሚያፋጥኑ ወሳኝ የፖሊሲ እርምጃዎችን በመተግበር የመሪነት ሚናዋን መወጣት እንዳለባትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፅንኦት ሰጥተዋል።
የዲጂታል ስርዓትን ለማስፋት በሚከናወኑ ስራዎች የመረጃ ሉዓላዊነትን ማስከበር ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተናግረዋል።
ይህም በውጭ ቴክኖሎጂዎች ላይ ያለንን ጥገኝነት ለመከላከል ያስችለናል ብለዋል።
ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማትና የክሂሎት ማበልጸጊያ ሥራዎች በአርዓያነት እየመራች መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመታት በፊት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አቋቁማ ወደ ስራ መግባቷንም ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ በታዳሽ ሃይል ልማትና ቴሌኮም ዘርፍ ያከናወነችው ስራም ለዲጂታል ምህዳሩ መስፋት አይነተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቅሰዋል።
እንደ ዲጂታል መታወቂያ እንዲሁም የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ያሉ መርሃ ግብሮችም ኢትዮጵያ ሕልሞችን ወደ ተጨባጭ ተግባር እያሸጋገረች መሆኗን ማሳያ መሆናቸውንም አንስተዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025