
አዲስ አበባ፤ግንቦት 8/2017(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው እና በወጭ ንግዱ ላይ በተከናወነው የቁጥጥር ስራ ከቁም እንስሳት እንዲሁም ስጋና ወተት የሚገኘውን ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደገው እንደሚገኝ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ስርዓቱ የተረጋጋ፣ ፍትሐዊና ተደራሽ እንዲሆን እንዲሁም የወጪና ገቢ ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ የማረጋገጥ ተግባር በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወንድሙ ፍላቴ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ ኢትዮጵያ ቁም እንስሳት፣ ስጋና የወተት ምርቶችን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከዘርፉ የውጭ ምንዛሬ በማግኘት ላይ ትገኛለች፡፡
በዘርፉ በተከናወኑ ከፍተኛ ስራዎችም በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 406 ሺህ የቁም እንስሳትና 23 ሺህ 986 ቶን የስጋና ወተት ምርት በመላክ 128 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በቁም እንስሳት፣በስጋና ወተት እንዲሁም በመኖ ዘርፍ ለማግኘት የታቀደው ዕቅድ አፈጻጸም ከባለፈው አመት ሲነጻጸር በሁሉም መስክ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ይህም ለውጥ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የዶላር ምንዛሬ በገበያ እንዲወሰንና ላኪያዎችን ማበረታታቱ እንዲሁም በወጪና ገቢ ምርቶች ላይ የሚደረገው የምርት ጥራት ቁጥጥር ምክንያት የመጣ መሆኑን ተናግረዋል።
በሀገሪቱ ወጪና ገቢ ምርቶች ጥራት በመቆጣጠር የጥራት ማረጋገጫ ከሚሰጡ ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን አንዱ ነው።
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሀሚድ ጀማል በበኩላቸው፤ በዓለም ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ መሆን የሚቻለው የምርት ጥራትና ደህንነት መጠበቅ ሲቻል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በዚህም ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የቁም እንስሳትና ስጋ ምርቶች ጥራታቸውና ደህንነታቸው የጠበቁ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ የመስጠት ተግባር እያከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል።
በዚህም በህገ ወጥ መንገድ ሲወጡ የነበሩ እንስሳት በህጋዊ መንገድ እንዲወጡ ማስቻሉን አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ ስጋ አምራችና ላኪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ከሊፋ ሁሴን ፤ በዓለም ገበያ ውስጥ መዳረሻን ለማስፋትና ተወዳዳሪ ለመሆን ጥራት ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ጠቅሰው፥ማህበራቱ በዓለም አቀፍ የተቀመጡ የጥራት ደረጃን ተግባራዊ በማድረግ ላይ መሆናቸውን አብራርተዋል።
የምርት ጥራትን መጠበቅ በዓለም ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪነትን የሚጨምር ከመሆኑም ባለፈ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የሚታደርገውን ጥረት የሚደግፍ መሆኑም ተገልጿል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026