የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በኢትዮጵያ አስቻይ የህግ ማዕቀፎች ተግባራዊ መደረጋቸው ዲጂታል ኢትዮጵያ በመገንባት ሂደት ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል

May 21, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ግንቦት 12/2017(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ አስቻይ የህግ ማዕቀፎችና ቅንጅታዊ አሰራሮች ተግባራዊ መደረጋቸው ዲጂታል ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት ተጨባጭ ውጤት እንዲመዘገብ ማስቻሉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ።


የአይዲ ፎር አፍሪካ አለምአቀፍ አመታዊ ጉባኤ በኢትዮጵያ መካሄድ ጀምሯል።


ጉባኤው የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ለአካታች ዕድገት ያለውን ጠቀሜታና የአገራት አተገባበር ላይ የልምድ ልውውጥ የሚደረግበት ነው።


ኢትዮጵያም የዲጂታል መታወቂያ ትግበራዋን ለጉባኤው ተሳታፊዎች አቅርባለች።


የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያን ተግባራዊ ለማድረግ የህግ ማዕቀፎችን ከማዘጋጀት ጀምሮ የተለያዩ የፖሊሲና ስትራቴጂ በማዘጋጀት ወደ ስራ ገብታለች።


በተለይም ለዲጂታል መታወቂያ መደላድል የሚፈጥሩ የዲጂታል መሰረተ ልማቶች ግንባታ በመንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራቱንም አመልክተዋል።


በ2025 ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የዲጂታል ፖሊሲና ስትራቴጂ ተነድፎ ወደ ትግበራ መገባቱን ነው የተናገሩት።


ባለፋት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ስራዎች ዲጂታል ፖሊሲና ስትራቴጂ በመቅረጽ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራምን ተግባራዊ ለማድረግ የነበረውን ዝግጅትና ቁርጠኝነት አብራርተዋል።


የዲጂታላይዜሽን ግንባታ ሂደት እንጂ አንዴ የሚጠናቀቅ ስራ አለመሆኑን ጠቅሰዋል።


ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን ማድረግ አስቻይ ሁኔታዎችን ከመፍጠር ባለፈ የመንግስት ተቋማት በቅንጅት እየሰሩ መሆኑንም አንስተዋል።


በዚህም የመንግስትን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የማስተሳሰርና የአገልግሎት ጥራትና ቅልጥፍናን ማረጋገጥ መቻሉንም ጠቅሰዋል።


በዚህ ረገድም ዲጂታል መታወቂያ ለፋይናንስ አካታችነት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቅሰው፥ በተለይም በገጠር አካባቢ ያሉ ዜጎች የፋይናንስ አገልግሎትን በቀላሉ እንዲያገኙ ማስቻሉን አንስተዋል።


የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ በበኩላቸው፥ የዲጂታል ኢትዮጵያ ካውንስል ስራዎችን አብራርተዋል።


በዚህም ካውንስሉ ከመንግስት ተቋማት ባለፈ የግል ዘርፉን በማሳተፍ የተለያዩ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።


የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭን በማስተባበር በርካታ ዜጎች ዲጂታላይዜሽን ላይ መሰረታዊ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዮናስ አለማየሁ፤ አዲስ አበባን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተከናወነ ላለው ተግባር የዲጂታል መታወቂያ ተደራሽነት ትልቅ ድርሻ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።


በከተማዋ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ከማሟላት ባለፈ የዲጂታል መታወቂያ ላይ ትርጉም ያለው ስራ ተሰርቷል ብለዋል።


የልደት፣ የሞትና ሌሎች ወሳኝ ኩነቶችን በአጭር ጊዜ በመመዝገብ ዲጂታል ማንነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025