
ጅማ፤ ግንቦት 11/2017(ኢዜአ)፦ ባለፋት ዓመታት የተከናወነው የተቀናጀ አደጋ መከላከል እና መልሶ ማቋቋም ሥራ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) አስታወቁ።
በጅማ ከተማ በሌማት ትሩፉትና የምግብ ስርዓት ሽግግር እንዲሁም የአደጋ ሥራ አመራር ግምገማና የቀጣይ አቅጣጫ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር)፤ ባለፉት ዓመታት በተደረገ የተቀናጀ አደጋን የመከላከል ሥራ ተጨባጭ ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል።
በዚህም ከአራት ዓመት በፊት የነበረው የድጋፍ ፈላጊ ቀጥርን በከፍተኛ ሁኔታ ዝቅ ማድረግ መቻሉን ገልጸው፣ ተፈናቃዮችንም የመመለስ ሥራ በስፋት መከናወኑን ተናግረዋል።
ለአደጋ ጊዜ ፈጥኖ መድረስ እንዲቻል የመጠባበቂያ የምግብ ክምችት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ለዚሁ ይረዳ ዘንድ የክምችት አቅምን ለማሳድግ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

በየደረጃው ባሉ አመራሮች አስተባባሪነት እንደ ሀገር 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ምግብና የምግብ ነክ ክምችት ለመያዝ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል።
የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን ለመከላከልና ፈጥኖ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ በራስ አቅም የተገነባ የትብብርና የቅንጅት ስራ እንደሚጠናከርም አመልክተዋል።
በተለያየ ጊዜ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ የደረሰባቸውን ወገኖች በዘላቂነት ማቋቋም የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ መቆየታቸውንም ኮሚሽነሩ አክለዋል።
በተለይም ህብረተሰቡ እርዳታ ጠባቂ እንዳይሆንና ሰርቶ መለወጥ እንዲችል የግንዛቤ ማሳደጊያ ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልጸው፣ ለዚህም ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ ነው ብለዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026