
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2017(ኢዜአ)፦ ግብርናውን በማዘመን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ለማጎልበት በጥናትና ምርምር እያከናወነ ያለውን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።
የዩኒቨርሲቲው አመታዊ የምርምር ሳምንት “መጻኢውን እንመግብ፣ በኢትዮጵያ ዘላቂ የምግብ ዋስትናን ከአዳዲስ ቴክኖሎጂና ፈጠራዎች ጋር ማስተሳሰር” በሚል መሪ ሃሳብ ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንስሳት ህክምና እና ግብርና ኮሌጅ ተጀምሯል።
የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ወራሽ ጌታነህ በመክፈቻ መርሃ-ግብሩ እንዳሉት ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን ለመቻል እያከናወነች ያለውን ተግባር ለሚደግፉ የምርምርና ቴክኖሎጂ ውጤቶች ትኩረት ተሰጥቷል።

የግብርናው ዘርፍ በሀገር ምጣኔ ሃብት እድገት፣ በስራ እድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ያለውን ጉልህ ሚና የበለጠ ለማሳደግ በምርምርና ቴክኖሎጂ መደገፍ ተገቢ መሆኑንም ገልጸዋል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ ተሳትፎ ቅድሚያ ከሰጣቸው ስምንት የምርምር አጀንዳዎች መካከል የመጀመሪያው መሆኑን ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው ከበጀቱ እስከ 10 በመቶ ለምርምርና ፈጠራ ለማዋል እየሰራ እንደሚገኝም ጨምረው ገልጸዋል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንደ ሀገር ግብርናውን በማሸጋገር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተተገበሩ የሚገኙ መርሃ ግብሮችን እውን ለማድረግ በጥናትና ምርምር እያከናወነ ያለውን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና እና ግብርና ኮሌጅ ዋና ዲን ሒካ ዋቅቶሌ(ዶ/ር) በበኩላቸው ኮሌጁ ኢትዮጵያ ያላትን የእንስሳት ሃብት በአግባቡ ጥቅም ላይ እንድታውል ዩኒቨርሲቲው ምርምሩን እያሰፋ ይገኛል ብለዋል።

ድህነትን ለማጥፋትና ርሃብን ለማስወገድ የተቀመጡ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ምርምርና ፈጠራ ትልቁን ሚና እንደሚጫወቱ የተናገሩት ደግሞ በኢትዮጵያ የአለም የምግብና እርሻ ድርጅት የቴክኒክ አማካሪ ጀምስ ብዊራኒ ናቸው።
ኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ምርትና ምርታማነት ለመጨመር ተግባራዊ ያደረገቻቸው የቴክኖሎጂና ምርምር ውጤቶች ወደ ውጭ የምትልካቸው ምርቶች መጨመር መቻሏ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

በምርምር ሳምንቱ የምርምርና ቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለጎብኚዎች ካቀረቡት መካከል በእንስሳት ህክምና እና ግብርና ኮሌጅ የእንስሳት ጤና ባለሙያ ከፍ ያለው ሚደቅሳ በአካባቢው የእንስት ጤናን በመጠበቅ እየተሰሩ የሚገኙ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
የጥናትና ምርምር ሳምንቱ የምርምርና ቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለጎብኚዎች በማቅረብ እስከ ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚቆይም ተገልጿል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026