የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ምርታማነትን በማሳደግ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል

May 21, 2025

IDOPRESS

ጅማ፣ግንቦት 12/2017(ኢዜአ)፡- መንግስት ምርታማነትን በማሳደግ የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ለሚያስችሉ ተግባራት ትኩረት መስጠቱን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕእረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።

ዓለም አቀፍ የንብ ቀንና 2ኛው ዘላቂ የንብ ማነብና እጽዋት ተራክቦ ኮንፈረንስ በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በተለይም ዓለም አቀፍ የንብ ቀን "ንቦችን እንጠብቅ" በሚል መሪ ሀሳብ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት እየተከበረ ነው።

አቶ አደም ፋራህ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ፤ መንግስት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ላይ በትኩረት እየሰራ ነው ።

የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብርም ዋንኛ አቅጣጫ ተደርጎ እየተተገበረ መሆኑን ጠቁመው፤ መርሃ-ግብሩ ለንብ ማነብና ለማር ምርታማነት እያበረከተ ያለውን አሰተዋጽኦ ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱንም አስታውቀዋል ።


የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) በበኩላቸው አካባቢን በመንከባከብ የንቦችን ደህንነት በመጠበቅ የማር ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በንብ መንጋ ብዛትና በማር ምርት ከአፍሪካ አንደኛ መሆኗን ጠቅሰው ዘርፉ በዘመናዊ የማር አመራረት እየተለወጠ ነው ብለዋል።

የማር አመራረትን ለማዘመን በተሰጠው ትኩረት ባለፉት ዘጠኝ ወራት እንደ ሀገር 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዘመናዊ ቀፎ መሰራጨቱንና 250ሺህ ቶን የማር ምርት መገኘቱን አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ በእንስሳት ሀብቷና በተፈጥሮ በታደለችው የአየር ጸባይ ለማር ምርት ምቹ በመሆኗ ከዘርፉ የተሻለ ተጠቃሚ ለመሆን በትጋት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025