የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የእንስሳትና ሰብል ምርታማነትን ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው - አቶ አደም ፋራህ

May 21, 2025

IDOPRESS

ጅማ፤ ግንቦት 12/2017(ኢዜአ)፦ የእንስሳትና ሰብል ምርታማነትን ይበልጥ በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማጎልበት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ።

የንቦች ቀን እየተከበረ ሲሆን በዚህም በጅማ ዞን ማና ወረዳ የዘመናዊ ቀፎ የማር ክላስተር ተጎብኝቷል።


አቶ አደም በጉብኝቱ ወቅት እንዳመለከቱት፤ ግብርናውን አጠናክረን ከውጭ የሚገባን ምርት በሀገር ውስጥ ለመተካት ውጤታማ ስራ እየተከናወነ ነው።

በግብርናው ዘርፍ ብዛት እና ጥራት ያለውን ምርት ይበልጥ በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ መልክዓ ምድሯ እና የአየር ጸባይዋ ለማር ምርት የተመቸ በመሆኑ ማርን በብዛትና በጥራት በማምረት ለውጭ ገበያ የማቅረቡ ስራ መጠናከር ያለበት ነው ብለዋል።

የማር ምርትን በጥራት አዘጋጅቶ ወደ ውጭ የመላክና የገበያ ትስስር መፍጠር ለሀገር ከፍተኛ የገቢ ምንጭ በመሆኑ በዚህ በኩል ጥሩ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የሌማት ትሩፋት አንዱና ዋነኛው ዓላማ የተሟላ የአመጋገብ ስርዓት ማምጣት ሲሆን በቀላሉ በጓሮ በሚለሙ የምግብ ዓይነቶች በመተግበር በማር፣ በወተት፣ በዶሮ ማርባት እና በእንቁላል እየተተገበረ መሆኑን ተናግረዋል።

ከማር ምርት በተጨማሪ በመስኖ ስንዴ ምርት፣ በሩዝ እና በፍራፍሬ ልማት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል።

መንግስት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ የሚያደርግ የግብርና ልማትን የሚያበረታታ በመሆኑ በየደረጃው ያሉ አካላት ለግብርናው ምርታማነት በትኩረት መስራት አለባቸው ብለዋል።


በጉብኝቱ የተሳተፉት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብና የእርሻ ድርጅት የአፍሪካ ተወካይ ዳይሬክተር ጀነራል አበበ ሀይለገብርኤል በበኩላቸው፤ የንቦች ቀን መከበሩ ለንቦች እና ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ ያደርጋል ነው ያሉት።

ንቦች የማር ምርት ከመስጠት ያለፈ ሚና ያላቸው በመሆኑ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለደን እንክብካቤና ለአረንጓዴ ልማት መነቃቃት ይፈጥራል ነው ያሉት።

በጅማ ዞን ማና ወረዳ በተደረገው ጉብኝትም የተመለከቱት የዘመናዊ ቀፎ የማር ልማት የሚበረታታ እና መስፋት ያለበት ተሞክሮ ሆኖ እንዳገኙት ጠቅሰዋል።

በጉብኝቱ ከዘመናዊ ቀፎ የማር ምርት በተጨማሪ የአቮካዶና የሙዝ ተክሎች ልማትም የተጎበኙ ሲሆን የአካባቢው አስተዳደርና የዘርፉ ባለሙያዎችም ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025