የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ የተገኙ ስኬቶችን በማስፋት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መስራት ይገባል

May 21, 2025

IDOPRESS

ጋምቤላ፤ግንቦት 12/2017(ኢዜአ)፦በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተለያዩ ዘርፎች የተገኙ ስኬቶችን በማስፋት የህዝብን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ተግቶ መስራት እንደሚገባ ተመላከተ።


የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶችን የዘጠኝ ወራት የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈፃጸም ገምግመዋል።


በምክር ቤቱ የሰው ሃብት፣የማህበራዊ ልማትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጋትሉዋክ ጋች እንደገለጹት፥ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በትምህርት ለትውልድ፣ በተማሪዎች ምገባና በሌሎች የትምህርት ልማት ስራዎች አበረታች ተግባራት ተከናውነዋል።


በቀጣይም ክልላዊና ሀገራዊ ፈተናዎች የሚሰጡበት ወቅት በመሆኑ የትምህርት ሴክተሩ ጥራትን ለማረጋገጥና የክልሉ ተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ሲያከናውናቸው የነበሩ ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።


በጤናው ዘርፍም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ድንገተኛና ተላላፊ በሽታዎችን በመከላከሉ ረገድ ስኬታማ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመው፥ በቀጣይም የክረምቱን መግቢያ ተከትሎ የወባ በሽታ እንዳይስፋፋ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።


የምክር ቤቱ የግብርና፣የመስኖና ቆላማ አካባቢ እና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዳዊት ድርኪያ በዘጠኝ ወራቱ የመስኖ መሰረተ ልማቶችን በማስፋት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ የተከናወኑ ስራዎች አበረታች ናቸው ብለዋል።


በአንፃሩ የግብርና ልማት ጣቢያ ሰራተኞች በስራ ገበታ ላይ ያለመገኘትና በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ረገድ ክፍተቶች መታየታቸውን ጠቁመው፥ በቀጣይ በተጠቀሱት ውስንነቶች ዙሪያ በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።


እንዲሁም በቀጣይ የመኸር ግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራዎች የሚከናወኑበት ጊዜ በመሆኑ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ወደ አርሶና አርብቶ አደሩ ዘልቀው በመግባት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።


በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ዘላቂ ሰላምና የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ በኩል ስኬታማ ስራዎች መከናወናቸውን የገለጹት ደግሞ የምክር ቤቱ የህግ፣ የፍትህና የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኡፓራ አጉዋ ናቸው።


በቀጣይ የተገኘውን ሰላም በማጽናት የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማፋጠን በትኩረት መስራት እንደሚገባም አቶ ኡፓራ ተናግረዋል።


የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ከትናንት ጀምሮ ለሁለት ቀናት ሲያካሄድ የቆየው የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ማምሻውን ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025