ጎንደር/ገንዳ ውሃ፤ግንቦት 12/2017 (ኢዜአ)፦የግብር ክፍያ ሥርዓቱን ከሙስናና ብልሹ አሰራር የጸዳ ለማድረግ የተጀመረው የዲጂታል አሰራር በወረዳ ደረጃም እንዲተገበር በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጠየቁ።
"ለሁለንተናዊ ብልጽግና የንግዱ ማህበረሰብ ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ በጎንደር እና በመተማ ከተሞች ከንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሄዷል።
በጎንደር ከተማ በተካሄደ መድረክ የተሳተፉት አቶ ጎበዜ መሀመድ፤ በክልሉ የተጀመረው ዲጂታል የግብር ክፍያና የንግድ ምዝገባ አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ወደ ወረዳዎች በፍጥነት ተደራሽ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።
ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥን መተግበር ለንግዱ ማህበረሰብም ሆነ ለመንግሥት የግብር አሰባሰብ መቀላጠፍ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የአገልግሎቱ በቴክኖሎጂ መደገፍ የነጋዴውን ተወዳዳሪነት ከማሳደግ ባለፈ የመልካም አስተዳደር ቅሬታን መፍታት እንደሚያስችል የተናገሩት ደግሞ አቶ ለማ ጌታነህ ናቸው።
በተለይ የመሰረተ ልማት አገልግሎቶችን በወረዳዎች በማሟላት የንግዱን ስርዓት ማዘመን ላይ ይበልጥ ሊተኮር ይገባል ብለዋል።
ሌላው ተሳታፊ አቶ ሰዒድ መሀመድ በበኩላቸው፥ ህገ ወጥ ንግድን ለመከላከል የተጀመረው ጥረት መጠናከር እንዳለበት ተናግረዋል።
ቀጣይነት ላለው የኢኮኖሚ እድገት የድርሻቸውን እንደሚወጡ የገለጹት ደግሞ በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ነዋሪ አቶ አደም ይመር ናቸው።
ለተግባራዊነቱም ህጋዊነትን የተላበሰ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲጠናከር የበኩላቸውን እንደሚወጡ አክለዋል።
የመተማ ዮሐንስ ከተማ ነዋሪ አቶ አስማማው ሲሳይ በበኩላቸ፥ የከተሞች እድገትና ውበት ነጋዴውን የሚያነቃቁ ናቸው ብለዋል።
የከተማዋን እድገት ለማስቀጠል ሰላም ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፥ ለሰላምና ጸጥታ መከበር ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
በተለያዩ ሴክተሮች የተጀመረው ዲጂታል አሰራር በሁሉም መዋቅሮች መስፋፋት እንዳለበት ጠቁመዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ፥ የንግዱ ማህበረሰብ የቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን የተጀመሩ የተቋማት የሪፎርም ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
በክልሉ ሰላምን በዘላቂነት በማስፈን ህዝቡን በኢኮኖሚና በማህበራዊ ልማት ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች እንደሚጠናከሩም ተናግረዋል።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አወቀ አስፈሬ እንዳሉት፤ የንግዱን ማህበረሰብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችና ቅሬታዎች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ነው።
ጽንፈኛው ተሽከርካሪዎችን በማቃጠል ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ጠቁመዋል።
ችግሩን ለመፍታት በሚደረገው ጥረትም የንግዱ ማህበረሰብ የበኩሉን እንዲወጣም አሳስበዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዳርጌ ጌጡ እንዳሉት፤ የአካባቢውን ሰላም ለማጠናከር በሚከናወኑ ሥራዎች የንግዱ ማህበረሰብ ከመንግስት ጎን በመሆን የጎላ ሚና ማበርከት ይኖርበታል።
በምክክር መድረኮቹ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።
#Ethiopian_News_Agency
#ኢዜአ
#Ethiopia
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025