የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በኢትዮጵያ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘላቂ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሒሳብና ሳይንስ ትምህርቶች ላይ ማተኮር ይገባል- ምሁራን

May 26, 2025

IDOPRESS

ዲላ፤ ግንቦት 14/2017 (ኢዜአ)፡-በኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂን ዘላቂ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ለሒሳብና ሳይንስ ትምህርቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የዘርፉ ምሁራን ገለጹ።

በዲላ ዩኒቨርሲቲ 8ኛው ዓለም አቀፍ የሒሳብና ሳይንስ ትምህርት አውደ ጥናትና 2ኛው አገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድር እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የተገኙ የሀገር ውስጥና የውጭ የዘርፉ ምሁራን እንዳሉት፤ በሒሳብ ትምህርት ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎች በማውጣት በዲጂታል ቴክኖሎጂ ረገድ ያለውን አቅም ለመጠቀም በቅንጅት ሊሰራ ይገባል።

"ሒሳብ ለማህበረሰብ ጥቅም" በሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሙሉጌታ አጥናፉ እንዳሉት ዲጂታል ቴክኖሎጂ የሒሳብ ቀመር ውጤት ነው ብለዋል።


ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በኮዲንግና መሰል ዲጂታል ዘርፎች በርካታ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑን ጠቅሰው በዘርፉም ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሒሳብን ከመማሪያ ክፍል ወደ ማህበረሰብ ለውጥ ማሸጋገር ይገባል ብለዋል።

በተለይ ምሁራን በዘርፉ በታችኛው እርከን የሚስተዋሉ የአመለካከት፣ የግብዓትና የተግባር ማነቆዎችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊፈቱ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በታችኛው እርከን የሚገኙ ተማሪዎች የሒሳብ ትምህርት ዝንባሌ ለማዳበር ወርደው መስራት እንዳለባቸው ያነሱት ደግሞ በአሜሪካ የሮዋን ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር አብዱልቃድር ሀሰን ናቸው።


ይህም የሰለጠነው አለም በስፋት የሚጠቀምበት ስርዓት መሆኑን አንስተው የትምህርት ጥራትን ከማሻሻል ባለፈ ከስር ጀምሮ ታዳጊዎችን በሒሳብ ክህሎት ለማብቃት አጋዥ መሆኑን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ሒሳብ ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ሳሙኤል አሰፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው ሒሳብ የቁጥር ቀመር ብቻ ሳይሆን ችግርን የሚፈታና የፈጠራ አቅምን ለማዳበር የሚያስችል ክህሎት ነው ብለዋል።

በመሆኑም ማህበሩ በአገር አቀፍ ደረጃ በሒሳብ ትምህርት ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎች ለማፍራት ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።


በዚህም በአፍሪካ ደረጃ ኢትዮጵያን በሒሳብ ትምህርት የሚወክሉ ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት መቻሉን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው በሒሳብና ሳይንስ ትምህርቶች ላይ ውጤት ተኮር ተግባራትን እየከናወነ ነው ያሉት ደግሞ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ኤልያስ ዓለሙ (ዶ/ር) ናቸው።

በተለይ በዩኒቨርሲቲው የፈጠራ ስራዎች ማበልጸጊያ ማዕከል በየዓመቱ በታችኛው እርከን የሚማሩ ተማሪዎችን ተግባር ተኮር ትምህርትና ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።


በተጨማሪም በአካበቢው በሚገኙ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዲጂታልና ቨርቹዋል ቤተ-ሙከራዎችን በማደራጀት ለሒሳብ ትምህርት ልዩ ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች ለማፍራት በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በአውደ ጥናቱ ላይም ጥናታዊ ጽሑፎች በአገር ውስጥና በውጭ ምሁራን እየቀረቡ ሲሆን ከትምህርት ሚኒስቴርና ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተወጣጡ ምሁራንና ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025