ሶዶ፤ግንቦት 16/2017 (ኢዜአ)፦በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ባለሀብቶች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ለመፍታት በተሰራው ስራ አበረታች ውጤቶች መመዝገቡን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ አስታወቁ።
ርዕሰ መስስተዳድሩ በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን በተመለከቱበት ወቅት እንዳሉት፥ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ ወዲህ ባለሀብቶችን በማወያየት ለስራቸው ማነቆ የሆኑ ጉዳዮችን ለመፍታት ሲሰራ ቆይቷል።
በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ያሉ ጸጋዎችን አሟጦ በመጠቀም የምርት መጠንና ጥራትን አሳድጎ ከውጭ የሚገባውን ምርት በሀገር ውስጥ ለመተካት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዘርፉ የተፈጠረውን መነቃቃት ለማስቀጠል ባለሀብቱ የሚያነሳውን ጥያቄ ለመፍታት የክልሉ መንግስት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ባለፉት 10 ወራት በክልሉ 13 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ምርት ተመርቶ ለውጭ ገበያ መቅረቡን የተናገሩት ደግሞ የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ቦጋለ ቦሼ (ዶ/ር) ናቸው።
በተያዘው ዓመትም 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለው ተኪ ምርት መመረቱንም አስታውቀዋል።
ጉብኝቱ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ባለሀብቶች የሚያነሱትን ችግር በመመልከት የገበያ፣ የአቅርቦት እና የሃይል እንዲሁም ሌሎችን ችግሮች ለመፍታት ያለመ መሆኑንም ገልጸዋል።
በዱቄትና ዳቦ ማምረት ስራ የተሰማራው የኖሚና ትሬዲንግ ባለቤት አቶ አወል ሸረፈዲን፤ በ2008 ዓ.ም በ70 ሚሊዮን ብር ካፒታል የጀመሩት ስራ አሁን ወደ ግማሽ ቢሊዮን ብር ማደጉን ተናግረዋል።
ፋብሪካው ለ270 ሰዎች የስራ ዕድል መፍጠሩንና ዱቄት፣ ዳቦ፣ ኬክና ሌሎች ምርቶችን ለተጠቃሚዎች እያቀረበ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
በቀጣይ ፖስታ እና ማኮሮኒ ለማምረት የማስፋፊያ ስራ መጀመራቸውን ገልጸው፥ ለስራው ስኬታማነት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
በሳሙና ማምረት ስራ ላይ የተሰማሩት አቶ ኤልያስ ኦጃሞ በበኩላቸው፥ ስራውን በ1 ሚሊዮን ብር መጀመራቸውን ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት ካፒታላችን ከ50 እስከ 60 ሚሊዮን ይደርሳል ያሉት ባለሀብቱ፥ ፋብሪካው ለ60 ሰራተኞች ቋሚና ጊዜያዊ ስራ መፍጠሩን ተናግረዋል።
ለፋብሪካው የጥሬ እቃዎች ማምረቻና ለካርቶን ዝግጅት የሚሆን ተጨማሪ የማስፋፊያ ቦታ ጠይቀው ምላሽ እየተጠባበቁ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
የማስፋፊያ ስራው ሲጠናቀቅ ከ200 ለሚልቁ ሰዎች የስራ ዕድል ይፈጠራል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025