ሚዛን አማን፤ ግንቦት 17/2017 (ኢዜአ)፡-የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እያሳደገው መምጣቱን በሸካ ዞን በዘርፉ የተሰማሩ የማሻ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
በዶሮ እርባታ የተሰማራው ወጣት አማኑኤል ኃይሌ ባለፉት ሦስት ዓመታት ለሥጋና ለእንቁላል የሚሆኑ ዶሮዎችን ለገበያ እያቀረበ መሆኑን ተናግሯል።
ሥራውን ከጀመረ ወዲህ ከ14 ሺህ በላይ ታዳጊ ዶሮዎችን እንዳሰራጨና በአሁን ወቅትም 2ሺህ ዶሮዎች ለሽያጭ ማዘጋጀቱን ጠቅሷል።
በአካባቢው ገበያ ያለውን የእንቁላል ፍላጎት በመረዳት 1ሺህ የእንቁላል ጣይ ዶሮዎችን በማርባት ወደሥራው መግባታቸውን የተናገሩት ደግሞ ሌላው የከተማዋ ነዋሪ አቶ ብርሃኑ ሀይሌ ናቸው።
በማር ምርት ሥራ ላይ ከተሰማሩት መካከል ከ50 በላይ ዘመናዊ ቀፎዎችን በማዘጋጀት ንብ የማነብ ሥራ መጀመሩን የገለጸው ደግሞ ወጣት ታጠቅ ሠራዊት ነው።
ከአንድ ዘመናዊ የንብ ቀፎ 30 ኪሎ ግራም ማር በማግኘት ገቢውን ለማሳደግ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑንም ጠቁሟል።
የማሻ ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስማማው ታምሩ "በቤተሰብ ደረጃ የተሟላ ማዕድ እንዲኖር የሚያስችለውን የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ስኬታማ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ ነው" ብለዋል።
በከተማው ኢኒሼቲቩን አስፋፍቶ ለማስቀጠል የሌማት ትሩፋት መንደር የማደራጀት ተግባር እየተከናወነ መሆኑን አመልክተዋል።
የሸካ ዞን ግብርና፣ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ አቶ አዕምሮ ደሳለኝ በበኩላቸው እንዳሉት በዋና ዋና የሌማት ትሩፋት ዘርፎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ነው።
ለእዚህም በዞኑ በሦስት ወረዳዎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች ከ120 በላይ የሌማት ትሩፋት መንደሮች መደራጀታቸውን በማሳያነት ጠቅሰዋል።
እነዚህን መንደሮች ሞዴል ለማድረግ እንደሚሰራ ጠቁመው ለዚህም በዞኑ በኩል የሙያና የቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚደረግ አመልክተዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025