አዲስ አበባ፤ግንቦት 18 /2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በውሃ ሀብትና በኢነርጂ ዘርፍ ያላትን ሀብት ዘመኑን በዋጀ መልኩ ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ስራ እያከናወነች መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስቴሩ በውሃ እና ኢነርጂ ረቂቅ የፖሊሲ ሰነዶች ላይ ግብአት ለማሰባሰብ የሚያስችል ውይይት ከዘርፉ ተዋናዮች ብሎም አጋር አካላት ጋር አካሂዷል።
በመድረኩም ለተሳታፊዎቹ በውሃና ኢነርጂ ዘርፎች የተዘጋጁ ረቂቅ ፖሊሲዎች አጠቃላይ ይዘት እና እንደ ሀገር የሚኖራቸውን ፋይዳ በተመለከተ ገለፃ ተደርጓል።
የውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ ከውሀ ሀብት እንዲሁም ከኢነርጂው ዘርፍ እንደ ሀገር ማግኘት የሚገባትን ሁለንተናዊ ጥቅም ለማስገኘትና ዘርፉን በተጠናከረ መንገድ ለመምራት ፖሊሲ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህንንም እውን ለማድረግ እንደ ሀገር ለረጅም ዘመናት የሚያገለግሉ የውሀና የኢነርጂ ፖሊሲዎችን ዘመኑ በሚመጥን ደረጃ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።
በዚህም ሚኒስቴሩ የኢትዮጵያ ውሀ ሀብት ረቂቅ ፖሊሲ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ረቂቅ ፖሊሲዎቹም የውሀ ሀብትን ብሎም ኢንርጂን በተገቢው ጥቅም ላይ ለማዋልና ለማስተዳደር እንዲሁም በሀገሪቱ ፍትሀዊ ተደራሽነት በሚያረጋግጡ መልኩ ተዘጋጅቷል ብለዋል።
በውሀ እና በኢነርጂ መስኮች ላይ የሚከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እውን ለማድረግ መንግስት በሚሰራው ስራ ብቻ ዘርፉን ማጎልበት አዳጋች መሆን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ የወጡ ረቂቅ ፖሊሲዎች ዘርፉ የግሉን ባለሀብቶች የሚሳተፉበትን አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል።
ሚኒስትሩ አያይዘውም በኢነርጂው ዘርፍ ላይ ከፍትሃዊ ተጠቃሚነትና ከተደራሽነት አኳያ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በተዘጋጀው ረቂቅ ፖሊሲ ላይ የዘርፉ ተዋናዮች የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲጫወቱም ጠይቀዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሃላፊ ዳዊት ሃይሉ በሰጡት አስተያየት፥ የረቂቅ ፖሊሲው መዘጋጀት ሀገሪቱን ብሎም ማህበረሰቡ በዘርፉ ላይ ያለውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የምንሰራቸውን ተግባራቶች ጥራት ባለውና በተደረጀ መልኩ ማከናወን እንድንችል አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ህዝቡን የንጹህ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመረውንም እንቅስቃሴ ከማጠናከርም ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወትም አክለዋል።
ሌላኛው አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት በኤስኤንቪ የኔዘርላንድ ዴቨሎፕመንት ድርጅት የኢነርጂ ዘርፍ አማካሪ ሰለሞን አለሙ፥ እንደ ሀገር የኢነርጂውን ዘርፍ ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች ቢኖርም በስፋት እና ተደራሽ ከመሆን አንጻር ክፍተት እንደሚስተዋልበት ገልጸዋል።
ነገር ግን አሁን ላይ የዚህ ረቂቅ ፖሊሲ መዘጋጀቱ ይህንን ክፍተት ለመሙላት እንደሚያግዝ ገልጸው ድርጅቱም በዚህ ላይ የሚጠበቅበትን ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በምክክር መድረኩ ላይ በውሃ እና ኢነርጂ በውሃና ኢነርጂ ዘርፎች የተዘጋጁ ረቂቅ ፖሊሲዎች ዙሪያ የመወያያ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025