አዲስ አበባ፤ግንቦት 20/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ዘርፍ ነገን ታሳቢ ያደረገ ስራ እየሰራች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል።
ኢንስቲትዩቱ በተቋቋመ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከከርሰ ምድር እስከ ስፔስ ድረስ ለልማት የሚያስፈልጉ መረጃዎችን እያቀረበ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
በከርሰ ምድር ጥናትና ምርምር የከርሰ ምድር የውሃ ሃብት ያለባቸውን አካባቢዎች መለየት የሚያስችል ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሐይቆች ያሉበትን ሁኔታ የማጥናት እና የውሃ ሃብቶችን የመለየት ስራ እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።
በተጨማሪም በገጸ-ምድር ላይ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ሽፋን፣የውሃና የአፈር ፀባይ በመለየት ለልማት አመች የሆኑ ወሳኝ መረጃዎችን እያመነጨ መሆኑን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አክለውም፥ በኢንስቲትዩቱ በውሃና በመሬት ልማት ጥናትና መረጃ አያያዝ ተስፋ ሰጪ ዕውቀት እየተገነባ ነው ብለዋል።
ካርታን በማተም ዲጂታላይዝ ከማድረግ ባለፈ በመተግበሪያ ልማት ጭምር የሚደነቅ ስራ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
የኢንስቲትዩቱን መቋቋም ተከትሎ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የስፔስ ክለብን መቀላቀሏን ጠቅሰው፥ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሁለት ሳተላይቶችን ወደምህዋር ማምጠቋንም አውስተዋል።
በቀጣይም ሶስተኛውን ሳተላይት ለማምጠቅ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥በሰው ሃብት ልማት ላይ ተጨባጭ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል።
በዚህም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ከማስተማር ባለፈ ፍላጎትና ክህሎት ያላቸውን ህፃናትን የማብቃት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ይህም ነገን ታሳቢ ያደረገ ትጋት መሆኑን በማንሳት፣ለስራ ገበያው ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ማፍራት የሚያስችል አውድ እየተፈጠረ እንደሚገኝ በጉብኝታቸው መመልከታቸውን አስረድተዋል።
የእንጦጦ ኦብዞርቫቶሪ አቅምን በማሳደግ ከሀገር ውስጥ በተጨማሪ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር መስራት የሚያስችል አቅም መገንባቱንም ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ ተቋማት በኢንስቲትዩቱ መረጃዎች በመተማመን እየተጠቀሟቸው መሆኑን ጠቁመው፥በጥቂት ዓመታት ውስጥ ይህን መመልከት ደስታ የሚሰጥ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ትውልድን ለማስቀጠል ታስቦ ሊሰራ ይገባል በሚል መርህ የወል ሃብትና ተቋማትን በመገንባት ቀጣይነት ያለው የምርታማነት አቅምን ማሳደግ እንደሚገባም አንስተዋል።
የስፔስ ሳይንስ፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣የሳይበር ደኅንነትና የትምህርት ተቋማትም ሕፃናት ላይ በትኩረት ከሰሩ የሀገርን ህልም መፍታት ይችላሉ ብለዋል።
ኢትዮጵያ ተስፋ አላት ያሉት ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ፥ነገን አስባ ዛሬን በትጋት እየሰራች እንደምትገኝ አንስተዋል።
በሁሉም መስክ ለልጆቻችን የተሻለች ሀገር እየገነባን ነውም ብለዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025