የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ዩኒቨርሲቲው በጥናትና ምርምር ላይ በማተኮር ለትምህርት ጥራቱ መሻሻል አስተዋጽኦ እያረከተ ነው

Jun 3, 2025

IDOPRESS

ደሴ፤ ግንቦት 22/2017(ኢዜአ)፡- ወሎ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ የታገዘ ተግባር ተኮር ትምህርት ከመስጠት ባሻገር ለትምህርት ጥራቱ መሻሻል ጥናትና ምርምር ላይ በማተኮር አስተዋጽኦ እያረከተ መሆኑን አስታወቀ።

ዩኒቨርሲቲው 5ኛውን "የመምህራን፣ ትምህርትና ስነ ባህሪ" ሀገር አቀፍ ጥናትና ምርምር ጉባኤ በደሴ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡


በጉባኤው የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ብርሃን አስማሜ(ዶ/ር) እንደገለጹት ተቋሙ በቴክኖሎጂ የታገዘ ተግባር ተኮር ትምህርት በመስጠት ላይ አተኩሮ እየሰራ ነው።

ለመማር ማስተማር ስራው የሚያግዙ የተለያዩ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ የትምህርት ጥራትንን ለማረጋገጥ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

መምህራን ከተማሪዎች ጋር ያላቸውን ተግባቦት በማሳደግ፣ ክህሎትና እውቀታቸውን በማዳበር የተሳለጠ መማር ማስተማሩን ለማሳለጥ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።


በዩኒቨርሲቲው የመምህራን ትምህርትና ስነ-ባህሪ ተቋም ዲን ጌታቸው ጣሰው(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው በቴክኖሎጂ፣ በጥናትና ምርምር በመታገዝ ብቁ ዜጋ ለማፍራት እየሰራ ይገኛል።

በጉባኤው በመማር ማስተማሩ ዘርፍ ስምንት ጥናታዊ ጽህፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ጠቁመው፤ የጥናቶቹን ግኝቶች መሰረት በማድረግ ወደ ተግባር እንዲቀየሩ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡


የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የገጠር ትምህርት ቤቶችን ያማከለ የትምህርት ስርዓት መዘርጋት ይገባል ያሉት ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጅ መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር በላይ ተፈራ ናቸው፡፡

ዘመናዊውን የመማር ማስተማር ዘዴን ከሀገር በቀል እውቀት ጋር ጭምር በማጣጣም ባህሉንና እሴቱን የጠበቀ፣ በስነ ምግባር የታነጸ፣ በክህሎት የዳበር ትውልድ ማፍራት ይገባል ብለዋል፡፡


በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮምሽን የምርምር ሥራ አስፈጻሚ ፕሮፌሰር ያለው እንዳወቅ፤ በቴክኖሎጂ የታገዘ ተግባር ተኮር ትምህርትን በማስፈን የኢትዮጵያን እድገት ማፋጠን እንደሚገባ አመልክተዋል።

ይህምትውልዱ ጠቃሚ ሀሳብ ማፍለቅንና አብሮነትን የሚያጎለብት እንዲሆን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምርምር መደገፍም ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራንና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ሲሆን፤ ጥናታዊ ጽሑፎች እንደሚቀርቡም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሀዋሳን የቱሪዝም እና ኢንቨስትመንት ማዕከል የማድረግ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ

ሀዋሳ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ ሀዋሳ ከተማን በማልማት የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ማዕከልነቷን ይበልጥ ለማሳደግ የሚከናወኑ የልማት ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Jun 14, 2026

በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የመኸር እርሻ ለማልማት ከታቀደው ውስጥ 72 ከመቶ የሚሆነው መሬት በዘር ተሸፍኗል

ጋምቤላ፤ ሰኔ 3/2018(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የመኸር እርሻ ለማልማት ከታቀደው ውስጥ ከ72 በመቶ በላይ የሚሆነው መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ...

Jun 11, 2026

በዞኑ ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በተከናወነ የንብ ማነብ ስራ ወደ 3 ሚሊዮን ኪሎ ግራም የሚጠጋ የማር ምርት ተገኘ

ደብረ ማርቆስ ፤ግንቦት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በተከናወነ የንብ ማነብ ስራ ወደ 3 ሚሊዮን ኪሎ ግራም የሚጠጋ የማ...

Jun 4, 2026

በዲላ ከተማ የተዘጋጀው "ቡኖ - ማላ" ኤክስፖ ምርቶችንና የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስተዋወቅ አስችሏል

ዲላ፤ ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፡-ከ40 በላይ የንግድ ተቋማትና አጋር አካላት ተሳትፈውበት በዲላ ከተማ የተዘጋጀው "ቡኖ - ማላ" ኤክስፖ ምርቶችን እና የኢ...

May 25, 2026