
ጅማ፣ግንቦት 24/2017(ኢዜአ)፦በጅማ ከተማ 47 የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።
የጅማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀመር እንዳሉት፥ አስተዳደሩ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ በጥራት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ እየተደረገ ነው፡፡
ፕሮጀክቶቹ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባሻገር የከተማዋን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከልነቷን ይበልጥ ለማሳደግ የሚያግዙ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የግንባታ ስራቸው ከተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች መካከል ሼዶች፣ የኢንዱስትሪ ማእከሎች፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድና የኮሪደር ልማት ስራዎች ይገኙበታል፡፡
በመንግስት በጀትና በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነቡ እነዚሁ የልማት ፕሮጀክቶች በግንባታ ሂደታቸውም ከ12 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል መፍጠራቸውን አመልክተዋል፡፡
አስተያየታቸውን ከሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ኪሩቤል ታረቀኝ በሰጠው አስተያየት በከተማዋ በኮሪደርና በሌሎች የልማት ስራዎች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የስራ እድል መፈጠሩን ተናግሯል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁት የመሰረተ ልማት ስራዎች ከተማዋን ውብና ሳቢ እንድትሆን ከማድረግ ባለፈ የስራ ዕድል መፍጠራቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላው የከተማዋ ነዋሪ አቶ ጋሊ አባ ወሊ ናቸው።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026