የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ ለ180 ሺህ አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጥቷል - ቢሮው

Jun 3, 2025

IDOPRESS

ሚዛን አማን፤ግንቦት 24/2017 (ኢዜአ)፦በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ለ180 ሺህ አርሶ አደሮች በዘመናዊ የመሬት ልኬትና ሰርቲፍኬሽን ሥርዓት የተመዘገበ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።


በክልሉ ቤንች ሸኮ ዞን በሁለተኛ ደረጃ የመሬት ልኬትና ሰርቲፍኬሽን ሥራ መሬታቸውን ላስመዘገቡ አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የመስጠት መርሐ ግብር በደቡብ ቤንች ወረዳ ተካሄዷል።


የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በወረዳው ቂጤ ቀበሌ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት በክልሉ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዘርፍን ለማዘመን በርካታ ተግባራት ሲከናወኑ ቆይቷል።


በዚህም የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት መሠረት በማድረግ ረቂቅ ደንብ መዘጋጀቱን ጠቅሰው "በቅርቡ ጸድቆ ወደ ተግባር ይገባል" ብለዋል።


በክልሉ ባሉ 17 ወረዳዎች በተካሄደው ሁለተኛ ደረጃ የመሬት ልኬትና የይዞታ ማረጋገጫ ሰርቲፍኬሽን ሥራ ከ250 ሺህ በላይ መሬት መለካት መቻሉን ገልጸዋል።


በዚህም በዘመናዊ መንገድ ተለክቶ በዲጂታል ሥርዓት የተመዘገበውን የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ለ180 ሺህ አርሶ አደሮች መሰጠቱን ጠቅሰዋል።


አርሶ አደሮች ባስመዘገቡት ይዞታ ተፈጥሮን እየጠበቁ አልምተው ዓለም አቀፍ ገበያን መቀላቀል የሚያስችል ምርት በማምረት ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡም አሳስበዋል።


የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን መሬት የኢኮኖሚ ሁሉ መሠረት በመሆኑ በአግባቡ አስተዳድሮ መጠቀም ይገባል ብለዋል።


አሁን እየተሠራ ያለው ዘመናዊ የመሬት ልኬት ሥርዓት የመሬት ባለቤትነት ዋስትና ከማረጋገጥ ባሻገር የሴቶችን የባለቤትነትና የብድር አገልግሎት መጠቀም መብትን ያረጋገጠ ነው ብለዋል።


በዞኑ ደቡብ ቤንች ወረዳ ቂጤ ቀበሌ በመጀመሪያ ዙር ከተለካ መሬት ውስጥ ከ3 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች በዘመናዊ መንገድ ተመዝግቦ መሰጠቱን ተናግረዋል።


የይዞታ ማረጋገጫ ሰርቲፍኬት ከተረከቡ የቀበሌው አርሶ አደሮች መካከል ወይዘሮ ወርቄ ይሽጉ፥አዲሱ የምዝገባ ስርዓት ተጠቃሚነታችንን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ደስተኛ ነኝ ብለዋል።


ከዚህ ቀደም ስራ ላይ ሳይውል የቆየውን መሬትን አስይዞ የመበደር፣ በአግባቡ አልምቶ የመጠቀምና የመሳሰሉ መብቶችን እና ግዴታዎችን ያካተተ ሰርቲፍኬት መረከባቸውን ተናግረዋል።


የምዝገባ ስርዓቱ የወሰን ውዝግብና መሰል የባለቤትነት አለመግባባቶችን የሚቀርፍ ነው ያሉት ደግሞ አቶ ታደለ ሞሊሶ የተባሉ የቀበሌው አርሶ አደር ናቸው።


ከምንም በላይ በቴክኖሎጂ ተደግፎ በዘመናዊ መንገድ ተመዝግቦ ይዞታቸው መረጋገጡ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ገልጸው፥ ከማስመዝገብ ባሻገር በአግባቡ አልምተው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እንደሚጥሩም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025